Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 18:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፥ “ወጥ​ተህ ወደ ባሕሩ ተመ​ል​ከት” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ተመ​ል​ክቶ፥ “ምንም የለም” አለ። ኤል​ያ​ስም፥ “ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለስ” አለው። ብላ​ቴ​ና​ውም ሰባት ጊዜ ተመ​ላ​ለሰ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 አገልጋዩንም፣ “ውጣና ወደ ባሕሩ ተመልከት” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ተመለከተና፤ “በዚያ ምንም የለም” አለው። ኤልያስ ሰባት ጊዜ፣ “እንደ ገና ሂድ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 አገልጋዩን፥ “ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት!” አለው። አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ “ምንም ነገር አይታየኝም” አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ብላቴናውንም “ወጥተህ ወደ ባሕሩ ተመልከት፤” አለው። ወጥቶም ተመልክቶም፥ “ምንም የለም፤” አለ። እርሱም “ሰባት ጊዜ ተመላለስ፤” አለው። ብላቴናውም ሰባት ጊዜ ተመላለሰ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 18:43
11 交叉引用  

እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


አክ​ዓ​ብም ሊበ​ላና ሊጠጣ ወጣ። ኤል​ያ​ስም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱ​ንም በጕ​ል​በቱ መካ​ከል አቀ​ር​ቅሮ በግ​ን​ባሩ ወደ ምድር ተደፋ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ፥ “እነሆ፥ የሰው ጫማ የም​ታ​ህል ትንሽ ደመና ከባ​ሕር ውኃ ቋጥራ ስት​ወጣ አየሁ” አለ። እር​ሱም፥ “ወጥ​ተህ አክ​ዓ​ብን፦ ዝናብ እን​ዳ​ይ​ዝህ ሰረ​ገ​ላ​ህን ጭነህ ውረድ በለው” አለ።


ተመ​ል​ሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲ​ህና ወዲያ ተመ​ላ​ለሰ፤ ደግ​ሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕ​ፃኑ ላይ ተጋ​ደመ፤ ከዚ​ያም በኋላ ሕፃኑ ዐይ​ኖ​ቹን ከፈተ።


በማ​ለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማ​ለዳ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፥ እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለ​ሁም።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይቸኵላል፥ እርሱም አይዋሽም፣ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ታገሠው፣ እርሱ አይዘገይም።


ዘወ​ትር እን​ዲ​ጸ​ልዩ፥ እን​ዳ​ይ​ሰ​ለ​ቹም በም​ሳሌ ነገ​ራ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ዓ​ል​ትና በሌ​ሊት ወደ እርሱ ለሚ​ጮኹ ለወ​ዳ​ጆቹ አይ​ፈ​ር​ድ​ምን? ወይስ ቸል ይላ​ቸ​ዋ​ልን?


በጸ​ሎ​ትና በም​ልጃ ሁሉ ዘወ​ትር በመ​ን​ፈስ ጸልዩ፤ ከዚ​ህም ጋር ስለ ቅዱ​ሳን ሁሉ ለመ​ጸ​ለይ ሁል​ጊዜ ትጉ፤


ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት በታ​ቦቱ ፊት ይያዙ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፤ ካህ​ና​ቱም ቀንደ መለ​ከ​ቱን ይንፉ።


跟着我们:

广告


广告