Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 18:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ከዚያም ኤልያስ፣ “የበኣልን ነቢያት ያዟቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ፤ ሕዝቡም ያዟቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ አሳረዳቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ፤ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ኤልያስም “የባዓልን ነቢያት ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዘ። ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሾን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ኤልያስም “ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ!” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 18:40
17 交叉引用  

ኤል​ያ​ስም አክ​ዓ​ብን፥ “የዝ​ናቡ ውሽ​ን​ፍር እጅግ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው።


አክ​ዓ​ብም ኤል​ያስ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ት​ንም ሁሉ በሰ​ይፍ እንደ ገደ​ላ​ቸው ለሚ​ስቱ ለኤ​ል​ዛ​ቤል ነገ​ራት።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ።


ገለ​ልም ብለው አሳ​ለ​ፉ​አት፤ እር​ስ​ዋም ወደ ፈረሱ በር መግ​ቢያ ወደ ንጉሡ ቤት ሄደች፤ በዚ​ያም ገደ​ሉ​አት።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈ​ረ​ሱት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት።


“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ በቀር ለአ​ማ​ል​ክት የሚ​ሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥


ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሰቃያሉ።


ሲሣ​ራም ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡን ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


እኔም የኢ​ያ​ቢ​ንን ሠራ​ዊት አለቃ ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስ​ባ​ለሁ፤ በእ​ጅ​ህም አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።”


ከዱሮ ጀምሮ የታ​ወቀ ያ የቂ​ሶን ወንዝ፥ የቂ​ሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰ​ዳ​ቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በርቺ።


跟着我们:

广告


广告