Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 18:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ኤልያስም በሕዝቡ ፊት ቀርቦ፣ “በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉት እስከ መቼ ድረስ ነው? እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እግዚአብሔርን ተከተሉ፤ በኣል አምላክ ከሆነም በኣልን ተከተሉ” አለ። ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል አልመለሱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ኤልያስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ? እግዚአብሔር አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤ በኣል ግን አምላክ ቢሆን እርሱን ተከተሉ፤” አለ። ሕዝቡም አንዲት ቃል አልመለሱለትም።

参见章节 复制




1 ነገሥት 18:21
27 交叉引用  

ባቱ​ኤ​ልና ላባም መለሱ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጥ​ቶ​አል፤ ክፉ ወይም በጎ ልን​መ​ል​ስ​ልህ አን​ች​ልም።


ይሁ​ዳም አለ፦ “ለጌ​ታ​ችን ምን እን​መ​ል​ሳ​ለን? ምንስ እን​ና​ገ​ራ​ለን? ወይስ በምን እን​ነ​ጻ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን ኀጢ​አት ገለጠ። እነሆ፥ እኛም ጽዋው ከእ​ርሱ ዘንድ የተ​ገ​ኘ​በ​ትም ደግሞ ለጌ​ታ​ችን አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነን።”


አክ​ዓ​ብም ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢ​ያ​ቱን ሁሉ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ያን ባዩ ጊዜ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት እርሱ አም​ላክ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ ነው” አሉ።


እነ​ዚ​ህም አሕ​ዛብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈሩ ነበር፤ ደግ​ሞም የተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያመ​ልኩ ነበር፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ደ​ረጉ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ።”


አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ አንተ አም​ላክ ነህ፤ ይህ​ንም መል​ካም ነገር ለባ​ሪ​ያህ ተና​ግ​ረ​ሃል።


የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምና​ሴም ጸለየ እን​ዲ​ህም አለ፦


በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤ ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።


ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል።


በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፥


የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ።


ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ አብረው ተሰበሰቡ።


“መምህር ሆይ! ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት?” ብሎ ጠየቀው።


“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።


ሲነ​ጋም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ወደ እርሱ ጠራ​ቸው፤ ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ዐሥራ ሁለ​ቱን መረጠ፤ ሐዋ​ር​ያት ብሎም ሰየ​ማ​ቸው።


አን​ደ​በት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለ​ምም ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በኦ​ሪት ላሉት እንደ ተነ​ገረ እና​ው​ቃ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላክ እንደ ሆነና ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ እን​ድ​ታ​ውቅ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ልኩ ዘንድ ባት​ወ​ድዱ ግን፥ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በወ​ንዝ ማዶ ሳሉ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት፥ ወይም በም​ድ​ራ​ቸው ያላ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት ታመ​ልኩ እንደ ሆነ፥ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”


ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልኩ፤ እር​ሱም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ያድ​ና​ች​ኋል” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告