Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ኤል​ያ​ስም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ ዛሬ ለእ​ርሱ እገ​ለ​ጣ​ለሁ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኤልያስም፣ “በፊቱ የቆምሁት ሁሉን የሚገዛ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን፣ ዛሬ በአክዓብ ፊት በርግጥ እገለጣለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኤልያስም “ዛሬ እኔ ለንጉሡ ራሴን እንደምገልጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በጌታ ስም ቃል እገባልሃለሁ!” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኤልያስም “ዛሬ እኔ ለንጉሡ ራሴን እንደምገልጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሃለሁ!” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኤልያስም “በፊቱ የቆምሁት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔርን! እኔ ዛሬ ለእርሱ እገለጣለሁ፤” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 18:15
19 交叉引用  

ሰማ​ይና ምድር ዓለ​ማ​ቸ​ውም ሁሉ ተፈ​ጸሙ።


በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።


አሁ​ንም፦ ሄደህ ኤል​ያስ አለ ብለህ ለጌ​ታህ ንገር ትላ​ለህ፤ እር​ሱም ይገ​ድ​ለ​ኛል።”


አብ​ድ​ዩም ሄዶ አክ​ዓ​ብን ተገ​ና​ኘው፤ ነገ​ረ​ውም፤ አክ​ዓ​ብም ሮጦ ሄዶ ኤል​ያ​ስን ተገ​ና​ኘው።


ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


ለሌ​ቦች ዕረ​ፍ​ትን የሚ​ሰጥ እን​ዳለ የሚ​መ​ስ​ለው አይ​ኑር። የክ​ፋ​ቱስ ወጥ​መድ የማ​ይ​መ​ጣ​በት ማን ነው?


የአ​ን​በ​ሶች ግል​ገ​ሎች ያገ​ሣሉ፥ ይነ​ጥ​ቃ​ሉም፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምግ​ባ​ቸ​ውን ይሻሉ።


አን​ዱም ለአ​ንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምድር ሁሉ ከክ​ብሩ ተሞ​ል​ታ​ለች” እያለ ይጮኽ ነበር።


በዚ​ያም ቀን አድ​ን​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው ሰዎች እጅ አል​ሰ​ጥ​ህም።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ውና በአ​መ​ለ​ኳ​ቸው፥ በተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውና በፈ​ለ​ጓ​ቸው፥ በሰ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም በፀ​ሐ​ይና በጨ​ረቃ፥ በከ​ዋ​ክ​ብ​ትም፥ በሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ፊት ይዘ​ረ​ጓ​ቸ​ዋል፤ አያ​ለ​ቅ​ሱ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​ብ​ሯ​ቸ​ው​ምም፤ በም​ድ​ርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ።


መል​አ​ኩም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ቆ​መው ገብ​ር​ኤል ነኝ፤ ይህ​ንም እነ​ግ​ር​ህና አበ​ሥ​ርህ ዘንድ ወደ አንተ ተል​ኬ​አ​ለሁ።


በፊ​ትህ የሚ​ቆም የነዌ ልጅ ኢያሱ እርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባል፤ እር​ሱን አበ​ር​ታው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድ​ሪ​ቱን ያወ​ር​ሳ​ልና።


ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።


跟着我们:

广告


广告