Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በም​ድር ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዝናብ እስ​ከ​ሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አይ​ጨ​ረ​ስም፥ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አይ​ጐ​ድ​ልም።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር ለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮውም ዘይት አያልቅም።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ‘ጌታ ለምድሪቱ ዝናብ እስከሚሰጥበት ዕለት ድረስ፤ ከማድጋው ዱቄት አይጠፋም፤ ከማሰሮው ዘይት አያልቅም።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ‘እኔ እግዚአብሔር ዝናብን እስከማወርድ ድረስ ዱቄቱ ከማኖሪያው ዕቃ፥ ዘይቱም ከማሰሮው ከቶ አያልቅም’ ሲል ተናግሮአል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና ‘በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፤ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።’”

参见章节 复制




1 ነገሥት 17:14
11 交叉引用  

ኤል​ያ​ስም አላት፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እመኚ፤ አት​ፍሪ፤ ሄደ​ሽም እን​ዳ​ል​ሽው አድ​ርጊ፤ አስ​ቀ​ድ​መሽ ግን ከዱ​ቄቱ ለእኔ ታናሽ እን​ጎቻ አድ​ር​ገሽ አም​ጭ​ልኝ፥ ከዚ​ያም በኋላ ለአ​ን​ቺና ለል​ጅሽ አድ​ርጊ፤


እር​ስ​ዋም ሄዳ እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ እር​ስ​ዋና እርሱ ልጆ​ች​ዋም በሉ።


ከፈ​ፋው ትጠ​ጣ​ለህ፤ ቁራ​ዎ​ችም በዚያ ይመ​ግ​ቡህ ዘንድ አዝ​ዣ​ለሁ።” ሄደም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚህ ሸለቆ ሁሉ ጕድ​ጓድ ቈፍሩ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነገ በዚህ ጊዜ በሰ​ማ​ርያ በር፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብስ በአ​ንድ ሰቅል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄ​ትም በአ​ንድ ሰቅል ይሸ​መ​ታል” አለው።


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።


አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች፤ በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው።


跟着我们:

广告


广告