1 ነገሥት 16:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 በይሁዳም ንጉሥ በኢዮሳፍጥ በሁለተኛው ዓመት የዘንበሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 የይሁዳ ንጉሥ አሳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት፣ የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፣ በሰማርያም ሆኖ እስራኤልን ሃያ ሁለት ዓመት ገዛ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ኻያ ሁለት ዓመት ገዛ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 አሳ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ ኻያ ሁለት ዓመት ገዛ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 በይሁዳም ንጉሥ በአሳ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዖምሪ ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ የዖምሪም ልጅ አክዓብ በእስራኤል ላይ በሰማሪያ ኻያ ሁለት ዓመት ነገሠ። 参见章节 |
ዘንበሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በሰማርያም ቀበሩት፤ ልጁም አክአብ በፋንታው ነገሠ። 28 ‘ሀ’ ዘንበሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆነው የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ ነገሠ። በነገሠም ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጋዙባ የምትባል የሴላህ ልጅ ነበረች። 28 ‘ለ’ በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ጽድቅን ያደርግ ዘንድ ከእርስዋ ፈቀቅ አላለም። በተራሮች የነበሩትንም አማልክት አላስወገደም፤ ሕዝቡም በተራሮቹ ይሠዉላቸውና ያጥኑላቸው ነበረ። 28 ‘ሐ’ ኢዮሳፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የሠራው፥ የተዋጋውና ያደረገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ ነው። 28 ‘መ’ በአባቱም በአሳ ዘመን የነበረውን ርኵሰት ሁሉ ከምድር አስወገደ። በኤዶምም ንጉሥ አልነበረም። 28 ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወርቅና ብርን ሊያመጡለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተርሴስ መርከብ አሠራ፤ በጋስዮንጋቤር የነበረችው መርከብ ተሰብራለችና አልሄደችም። 28 ‘ረ’ የእስራኤልም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን፥ “አገልጋዮችህንና አገልጋዮቼን በመርከብ እንላክ” አለው። ኢዮሳፍጥም እንቢ አለ። 28 ‘ሰ’ ኢዮሳፍጥም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ። በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። በእርሱም ፋንታ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።