Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 16:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ዘን​በ​ሪም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፤ ልጁም አክ​አብ በፋ​ን​ታው ነገሠ። 28 ‘ሀ’ ዘን​በ​ሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆ​ነው የአሳ ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ነገሠ። በነ​ገ​ሠም ጊዜ ሠላሳ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ አም​ስት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጋዙባ የም​ት​ባል የሴ​ላህ ልጅ ነበ​ረች። 28 ‘ለ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ጽድ​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ ከእ​ር​ስዋ ፈቀቅ አላ​ለም። በተ​ራ​ሮች የነ​በ​ሩ​ት​ንም አማ​ል​ክት አላ​ስ​ወ​ገ​ደም፤ ሕዝ​ቡም በተ​ራ​ሮቹ ይሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውና ያጥ​ኑ​ላ​ቸው ነበረ። 28 ‘ሐ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ጋር የሠ​ራው፥ የተ​ዋ​ጋ​ውና ያደ​ረ​ገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው። 28 ‘መ’ በአ​ባ​ቱም በአሳ ዘመን የነ​በ​ረ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ከም​ድር አስ​ወ​ገደ። በኤ​ዶ​ምም ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም። 28 ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም ወር​ቅና ብርን ሊያ​መ​ጡ​ለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከብ አሠራ፤ በጋ​ስ​ዮንጋቤር የነ​በ​ረ​ችው መር​ከብ ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም። 28 ‘ረ’ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮቼን በመ​ር​ከብ እን​ላክ” አለው። ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንቢ አለ። 28 ‘ሰ’ ኢዮ​ሳ​ፍ​ጥም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ። በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ዖምሪ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ ልጁም አክዓብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ዖምሪ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዖምሪ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ አክዓብ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ዖምሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ ልጁም አክዓብ በፋንታው ነገሠ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 16:28
6 交叉引用  

ዘን​በ​ሪም ከዚ​ያች ተራራ ባለ​ቤት ከሴ​ሜር በሁ​ለት መክ​ሊት ብር የሳ​ም​ሮ​ንን ተራራ ገዛ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ ከተማ ሠራ፤ የሠ​ራ​ት​ንም ከተማ በተ​ራ​ራው ባለ​ቤት በሳ​ምር ስም ሰማ​ርያ ብሎ ጠራት።


የቀ​ረ​ውም ዘን​በሪ ያደ​ረ​ገው ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ጭከና፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የዘ​ን​በሪ ልጅ አክ​ዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ሃያ ሁለት ዓመት ነገሠ።


ባኦ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቴ​ር​ሳም ተቀ​በረ፤ ልጁም ኤላ በአሳ በሃያ ስድ​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ለአ​ክ​አ​ብም በሰ​ማ​ርያ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት፤ ኢዩም ደብ​ዳቤ ጽፎ፥ የአ​ክ​አ​ብን ልጆች ለሚ​ያ​ሳ​ድጉ፥ ለሰ​ማ​ርያ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ሰማ​ርያ ላከ።


አካ​ዝ​ያ​ስም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ ዕድ​ሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።


跟着我们:

广告


广告