Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በነ​ቢዩ በኢዩ አፍ በባ​ኦስ ቤት ላይ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚህ ሁኔታም በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ በተነገረው በእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የባኦስን ቤተ ሰብ ሁሉ ፈጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚህም ዓይነት ጌታ በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በነቢዩ ኢዩ አማካይነት በባዕሻ ላይ ባናገረው ትንቢት መሠረት ዚምሪ የባዕሻን ቤተሰብ በሙሉ ፈጀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12-13 ባኦስና ልጁ ኤላ ስለ ሠሩት ኀጢአት ሁሉ፥ በምናምንቴም ሥራቸው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ያስቆጡት ዘንድ እስራኤልን ስለ አሳቱበት ኀጢአት፥ በነቢዩ በኢዩ አማካይነት በባኦስ ላይ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ዘምሪ የባኦስን ቤት ሁሉ እንዲሁ አጠፋ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 16:12
11 交叉引用  

በባ​ሪ​ያ​ውም በነ​ቢዩ በአ​ኪያ እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እስ​ራ​ኤል ሁሉ ቀበ​ሩት፥ አለ​ቀ​ሱ​ለ​ትም።


አሳና የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ባኦስ በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ሲዋጉ ኖሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ ባኦስ እን​ዲህ ብሎ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ኢዩ መጣ።


ስለ​ዚ​ህም፥ እነሆ፥ ባኦ​ስ​ንና ቤቱን ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ ቤት​ህ​ንም እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት አደ​ር​ጋ​ለሁ።


በእ​ጁም ሥራ ያስ​ቈ​ጣው ዘንድ፥ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስላ​ደ​ረ​ገው ክፋት ሁሉ እር​ሱ​ንም ስለ ገደ​ለው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በባ​ኦ​ስና በቤቱ ላይ ወደ አናኒ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢዩ መጣ።


በአ​ገ​ል​ጋዩ በኤ​ል​ያ​ስም ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዱቄቱ ከማ​ድ​ጋው አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም፤ ዘይ​ቱም ከማ​ሰ​ሮው አል​ጐ​ደ​ለም።


በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ነቢዩ የአ​ናኒ ልጅ ኢዩ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ ንጉ​ሡ​ንም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ታግ​ዛ​ለ​ህን? ወይስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጠ​ላ​ውን ትወ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ስለ​ዚ​ህም ነገር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ቍጣ መጥ​ቶ​ብ​ሃል።


የቀ​ረ​ውም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገ​ሮች፥ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ሥ​ታት ታሪክ በጻ​ፈው በአ​ናኒ ልጅ በነ​ቢዩ በኢዩ ታሪክ ተጽ​ፈ​ዋል።


跟着我们:

广告


广告