Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አኪ​ያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመ​መው ልጅዋ ትጠ​ይ​ቅህ ዘንድ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ትመ​ጣ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም ለውጣ ወደ አንተ በገ​ባች ጊዜ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ በላት” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር ግን ለአኪያ፣ “እነሆ፤ የኢዮርብዓም ሚስት ስለ ታመመው ልጇ ልትጠይቅህ ሌላ ሴት መስላ ትመጣለችና እንዲህ ብለህ መልሳት” ብሎ ነገረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ይሁን እንጂ የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጇ ልትጠይቀው እንደምትመጣና ምን ሊነግራት እንደሚገባውም ጌታ አስቀድሞ ለነቢዩ አኪያ ገልጦለት ነበር። የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ሞከረች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ይሁን እንጂ የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጅዋ ልትጠይቀው እንደምትመጣና ምን ሊነግራት እንደሚገባውም እግዚአብሔር አስቀድሞ ለነቢዩ አኪያ ገልጦለት ነበር። የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ሞከረች፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም አኪያን “እነሆ፥ ስለ ታመመው ልጅዋ ትጠይቅህ ዘንድ የኢዮርብዓም ሚስት ትመጣለች፤ ሌላ ሴትም መስላ ተሰውራለችና በገባች ጊዜ እንዲህና እንዲህ በላት፤” አለው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 14:5
8 交叉引用  

ኢዮ​አ​ብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብል​ሃ​ተኛ ሴት አስ​መ​ጣና፥ “አል​ቅሺ፤ የኀ​ዘ​ንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይ​ትም አት​ቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እን​ደ​ም​ታ​ለ​ቅስ ሴት ሁኚ፤


እር​ስ​ዋም በደጅ ስት​ገባ አኪያ የእ​ግ​ር​ዋን ኮቴ ሰማ፤ እን​ዲ​ህም አላት፥ “የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ሚስት ሆይ፥ ግቢ! ስለ​ም​ንስ ራስ​ሽን ለወ​ጥሽ? እኔም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ንቅ ወሬ ይዤ ወደ አንቺ ተል​ኬ​አ​ለሁ።


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


跟着我们:

广告


广告