Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም አብያ በፋ​ን​ታው ነገሠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። እናቱ ናዓማ የተባለች አሞናዊት ነበረች። ልጁ አብያም በርሱ ፈንታ ነገሠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ አቢያ ተተክቶ ነገሠ። የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ አቢያ ተተክቶ ነገሠ። የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። ልጁም አብያም በፋንታው ነገሠ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 14:31
12 交叉引用  

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ሴቶ​ችን ይወድ ነበር፥ ከባ​ዕ​ዳን ሕዝ​ብም የፈ​ር​ዖ​ንን ልጅ፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ና​ው​ያ​ትን፥ ሶር​ያ​ው​ያ​ት​ንና ሲዶ​ና​ው​ያ​ትን፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ት​ንና አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ት​ንም፦ ሚስ​ቶ​ችን አገባ።


ሰሎ​ሞ​ንም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም ሮብ​ዓም በፋ​ን​ታው ነገሠ።


የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት የሮ​ብ​ዓም ልጅ አብያ በይ​ሁዳ ላይ ንጉሥ ሆነ።


አሳም እንደ አባ​ቶቹ አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ። ልጁም ኢዮ​ሣ​ፍጥ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ባደ​ረ​ገው በአ​ባቱ ኀጢ​አት ሁሉ ሄደ፤ ልቡም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ፍጹም አል​ነ​በ​ረም።


ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።


የሰ​ሎ​ሞ​ንም ልጅ ሮብ​ዓም ነበረ፤ ልጁ አቢያ፥ ልጁ አሳ፥ ልጁ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥


ሮብ​ዓ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ፤ ልጁም አብያ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ሰሎሞንም ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሣፍን ወለደ፤


“አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።


跟着我们:

广告


广告