Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 12:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ይህ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ያቀ​ርብ ዘንድ ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታ​ቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ለ​ሳል፥ እኔ​ንም ይወ​ጉ​ኛል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፣ እንደ ገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ይህ ሕዝብ መሥዋዕት ለማቅረብ ኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ የሚወጣ ከሆነ፥ እንደገና ልቡን ወደ ጌታው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ሊያዞር ነው። ከዚያም እኔን ይገድለኛል፤ ወደ ንጉሡም ወደ ሮብዓም ይመለሳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ይህ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም ቢወጣ፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ወደ ጌታቸው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሮብዓም ይመለሳል፤ እኔንም ይገድሉኛል፤” አለ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 12:27
14 交叉引用  

የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።


ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊት ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገ​ሮች ሁሉ ስለ መረ​ጥ​ኋት ከተማ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን ሁለት ነገድ ይቀ​ሩ​ለ​ታል፤


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በልቡ አለ፥ “እነሆ፥ ዛሬ መን​ግ​ሥት ወደ ዳዊት ቤት ይመ​ለ​ሳል።


“ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​መ​ል​ሳ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቢጸ​ልዩ፥


ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤ ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከነ​ገ​ዶ​ችህ ከአ​ንዱ ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ርብ፤ በዚ​ያም ዛሬ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው ስፍራ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ከበ​ግና ከላም መንጋ ሠዋ።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በመ​ረ​ጠው በዚያ ስፍራ ከግ​ብፅ በወ​ጣ​ህ​በት ወራት፥ ፀሐይ ሲገባ፥ ማታ ፋሲ​ካን ትሠ​ዋ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告