Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርን ከረ​ም​ማ​ቴር ወገን የኤ​ል​ያ​ዳሔ ልጅ ኤስ​ሮ​ምን የሲባ ንጉሥ ጌታ​ውን አድ​ረ​ዓ​ዛ​ርን ጠላት አድ​ርጎ በሰ​ሎ​ሞን ላይ አስ​ነሣ። ሰዎ​ችም ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ። የዓ​መ​ፁም አበ​ጋዝ እርሱ ነበር። ደማ​ስ​ቆ​ንም እጅ አደ​ረ​ጋት። በሰ​ሎ​ሞ​ንም ዘመን ሁሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ጠላት ሆነ። ኤዶ​ማ​ዊው አዴ​ርም ከኤ​ዶ​ም​ያስ ነገ​ሥ​ታት ዘር ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እግዚአብሔር ከኤዶም ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ኤዶማዊውን ሃዳድን በሰሎሞን ላይ አስነሣው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህም ጌታ የኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ ወገን የሆነውን ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህም እግዚአብሔር የኤዶም ንጉሣዊ ቤተሰብ ወገን የሆነውን ሀዳድን በሰሎሞን ላይ ጠላት አድርጎ አስነሣበት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እግዚአብሔርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር የኤዶምያስን ሰው ሃዳድን ጠላት አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣው።

参见章节 复制




1 ነገሥት 11:14
13 交叉引用  

ደግ​ሞም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊ​ት​ንም፥ “ሂድ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንና ይሁ​ዳን ቍጠር” ብሎ በላ​ያ​ቸው አስ​ነ​ሣው።


እኔም አባት እሆ​ነ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ልጅ ይሆ​ነ​ኛል፤ ክፉ ነገ​ርም ቢያ​ደ​ርግ፥ በሰ​ዎች በት​ርና በሰው ልጆች አለ​ንጋ እገ​ሥ​ጸ​ዋ​ለሁ፤


ነገር ግን ስለ ባሪ​ያዬ ስለ ዳዊ​ትና ስለ መረ​ጥ​ኋት ሀገሬ ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለል​ጅህ አንድ ነገድ እሰ​ጣ​ለሁ እንጂ መን​ግ​ሥ​ቱን ሁሉ አል​ከ​ፍ​ልም።”


ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከጌ​ታው ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር የኰ​በ​ለ​ለ​ውን የኤ​ል​ያ​ዳን ልጅ ሬዞ​ንን ጠላት አድ​ርጎ አስ​ነ​ሣ​በት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምድ​ያ​ምን በመ​ከ​ራው ቦታ እንደ መታው ጅራ​ፍን ያነ​ሣ​በ​ታል፤ ቍጣ​ውም በባ​ሕሩ መን​ገ​ድና በግ​ብፅ መን​ገድ በኩል ይሆ​ናል።


ለቍ​ጣዬ በትር ለሆኑ፥ ለመ​ዓ​ቴም ጨን​ገር በእ​ጃ​ቸው ላለ ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ወዮ​ላ​ቸው!


እነሆ፥ ብር የማ​ይ​ሹ​ትን፥ ወር​ቅም የማ​ያ​ም​ራ​ቸ​ውን ሜዶ​ና​ው​ያ​ንን በእ​ና​ንተ ላይ አስ​ነ​ሣ​ለሁ።


ኤዶ​ም​ያ​ስም ርስቱ ይሆ​ናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በኀ​ይል ያደ​ር​ጋል።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告