Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 10:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ያሠ​ራው የመ​ጠጫ ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ ኵስ​ኵ​ስ​ቱም የወ​ርቅ ነበረ፤ የሊ​ባ​ኖስ ዱር የተ​ባ​ለ​ውን የዚ​ያን ቤት ዕቃ ሁሉ በወ​ርቅ አስ​ለ​በ​ጠው። የብ​ርም ዕቃ አል​ነ​በ​ረም፤ በሰ​ሎ​ሞን ዘመን የብር ዋጋ ዝቅ​ተኛ ነበ​ርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ንጉሥ ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፤ በሰሎሞን ዘመን ብር ዋጋ እንደሌለው ስለሚቈጠር ከብር የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ንጉሡም ሰሎሞን የሚጠጣበት ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር የተባለውም ቤት ዕቃ ሁሉ ጥሩ ወርቅ እንጂ ብር አልነበረም። በሰሎሞን ዘመን ብር ከቶ አይቆጠርም ነበር።

参见章节 复制




1 ነገሥት 10:21
9 交叉引用  

ከጥ​ፍ​ጥ​ፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአ​ን​ዱም ጋሻ የገ​ባው ወርቅ ሦስት ምናን ነው፤ ንጉ​ሡም የሊ​ባ​ኖስ ዱር በተ​ባ​ለው ቤት ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።


በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም።


ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


የሊ​ባ​ኖስ ዱር ቤት የሚ​ባል ቤት​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም መቶ ክንድ፥ ስፋ​ቱ​ንም አምሳ ክንድ፥ ቁመ​ቱ​ንም ሠላሳ ክንድ አደ​ረገ፤ የዋ​ን​ዛም እን​ጨት በሦ​ስት ወገን በተ​ሠሩ አዕ​ማድ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ዕ​ማ​ዱም ላይ የዋ​ንዛ እን​ጨት አግ​ዳሚ ሰረ​ገ​ሎች ነበሩ።


“በእ​ው​ነቱ ብር የሚ​ወ​ጣ​በት ቦታ አለ፥ ወር​ቅም የሚ​ነ​ጠ​ር​በት ስፍራ አለ።


ጢሮስም ምሽግን ለራስዋ ሠርታለች፥ ብሩንም እንደ አፈር ጥሩውንም ወርቅ እንደ መንገድ ጭቃ አከማችታለች።


ልቡም እን​ዳ​ይ​ስት ሚስ​ቶ​ችን ለእ​ርሱ አያ​ብዛ፤ ወር​ቅና ብርም ለእ​ርሱ እጅግ አያ​ብዛ።


跟着我们:

广告


广告