Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመሞችና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን ያበረከተችለትን ያን ያህል ብዛት ያለው ቅመማ ቅመም ከዚያ በኋላ ከቶ አልመጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቁ ነበር፤ እርሷ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ንግሥተ ሳባ ያመጣችለትን ስጦታ ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን አበረከተችለት፤ ይኸውም ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና የከበረ ዕንቊ ነበር፤ እርስዋ ለሰሎሞን ያበረከተችው የሽቶ ብዛት ከዚያ በኋላ ከቀረበለት የሽቶ ገጸ በረከት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ የሽቱ ብዛት ከዚያ ወዲያ አልመጣም ነበር።

参见章节 复制




1 ነገሥት 10:10
12 交叉引用  

አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


በግ​መ​ሎ​ችም ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ጣች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ ነገ​ረ​ችው።


ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።


እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤ የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


እን​ደ​ዚህ ብዬ ብና​ገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የል​ጆ​ች​ህን ትው​ልድ በበ​ደ​ልሁ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ሙጫ፥ በዛ​ጎል ውስጥ የሚ​ገኝ ሽቱ፥ የሚ​ሸ​ት​ትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ፤ የሁ​ሉም መጠን ትክ​ክል ይሁን።


ወርቅና ብዙ ቀይ ዕንቍ ይገኛል፤ የዕውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።


ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


跟着我们:

广告


广告