Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ንጉ​ሡም እን​ዲህ ብሎ ማለ፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳ​ነኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከዚያም ንጉሡ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳናት ሕያው እግዚአብሔርን!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ንጉሡም፦ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ በሕያው ጌታ ቃል እገባለሁ!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በዚህም ጊዜ እንዲህ አላት፥ “ከደረሰብኝ መከራ ሁሉ በታደገኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም ቃል እገባልሻለሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ንጉሡም “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን!

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:29
19 交叉引用  

ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


ዳዊ​ትም በዚያ ሰው ላይ ተቈጣ፤ ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ይህን ያደ​ረገ ሰው ሞት የሚ​ገ​ባው ነው።


ዳዊ​ትም ለቤ​ሮ​ታ​ዊው ለሬ​ሞን ልጆች ለሬ​ካ​ብና ለወ​ን​ድሙ ለበ​ዓና እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው፥ “ነፍ​ሴን ከመ​ከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን!


ንጉ​ሡም ዳዊት፥ “ቤር​ሳ​ቤ​ህን ጥሩ​ልኝ” ብሎ መለሰ። ወደ ንጉ​ሡም ገባች፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆመች።


በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ጌታዬ፥ ይፈ​ል​ግህ ዘንድ ያል​ላ​ከ​በት ሕዝብ ወይም መን​ግ​ሥት የለም፤ ሁሉም፦ በዚህ የለም ባሉ ጊዜ አን​ተን እን​ዳ​ላ​ገኙ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን አም​ሎ​አ​ቸው ነበር።


አሁ​ንም ያጸ​ናኝ፥ በአ​ባ​ቴም በዳ​ዊት ዙፋን ላይ ያስ​ቀ​መ​ጠኝ፥ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ቤትን የሠ​ራ​ልኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዛሬ አዶ​ን​ያስ ፈጽሞ ይገ​ደ​ላል።


የሕ​ፃ​ኑም እናት፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም! አል​ተ​ው​ህም” አለች፤ ኤል​ሳ​ዕም ተነ​ሥቶ ተከ​ተ​ላት።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አል​ቀ​በ​ልም” አለ። ይቀ​በ​ለ​ውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ።


የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ግያዝ፥ “ጌታዬ ሶር​ያ​ዊ​ውን ይህን ንዕ​ማ​ንን ማረው፤ ካመ​ጣ​ለ​ትም ነገር ምንም አል​ተ​ቀ​በ​ለም፤ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በስ​ተ​ኋ​ላው እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም አን​ዳች እወ​ስ​ዳ​ለሁ” አለ።


ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?


ሁል​ጊ​ዜም የተ​ገ​ረ​ፍሁ ሆንሁ፥ መሰ​ደ​ቤም በማ​ለዳ ነው።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “የእ​ናቴ ልጆች ወን​ድ​ሞቼ ነበሩ፤ አድ​ና​ች​ኋ​ቸው ቢሆን ኖሮ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ አል​ገ​ድ​ላ​ች​ሁም ነበር” አለ።


እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


ሕዝ​ቡም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት ያደ​ረገ ዮና​ታን ዛሬ ይሞ​ታ​ልን? ይህ አይ​ሁን፤ ዛሬ ለሕ​ዝቡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከራሱ ጠጕር አን​ዲት በም​ድር ላይ አት​ወ​ድ​ቅም” አሉት። ሕዝ​ቡም ያን ጊዜ ስለ ዮና​ታን ጸለዩ፤ እር​ሱም አል​ተ​ገ​ደ​ለም።


ሳኦ​ልም የዮ​ና​ታ​ንን ቃል ሰማ፤ ሳኦ​ልም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳዊት አይ​ገ​ደ​ልም” ብሎ ማለ።


እነ​ሆም፦ ሂድ ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ፈልግ ብዬ ብላ​ቴ​ና​ውን እል​ካ​ለሁ፤ ብላ​ቴ​ና​ው​ንም፦ እነሆ፥ ፍላ​ጻው ከአ​ንተ ወደ​ዚህ ነው፤ ይዘ​ኸው ወደ እኔ ና ያል​ሁት እንደ ሆነ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ለአ​ንተ ሰላም ነውና ምንም ክፉ ነገር የለ​ብ​ህም።


跟着我们:

广告


广告