1 ነገሥት 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 የዳዊት አሽከሮችም፥ “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ልጅ ትፈለግለት፤ በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፥ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ትቀፈው፤ ታሙቀውም” አሉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ “ንጉሡን የምትንከባከብና የምታገለግል ወጣት ድንግል እንፈልግ፤ እርሷም ጌታችን ንጉሡ እንዲሞቀው በጐኑ ትተኛለች” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ስለዚህ ባለሟሎቹ “ንጉሥ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣልህ፤ ከአንተ ጋር ዐቅፋህ በመተኛት ታሞቅሃለች” አሉት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ባሪያዎቹም “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ትፈለግለት፤ በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፤ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ታሙቀው፤” አሉት። 参见章节 |