Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ነገሥት 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁ​ንም ነዪ፤ የል​ጅ​ሽን የሰ​ሎ​ሞ​ንን ነፍ​ስና የአ​ን​ቺን ነፍስ እን​ድ​ታ​ድኚ እመ​ክ​ር​ሻ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አሁንም የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት እንዴት ማዳን እንደምትችዪ ልምከርሽ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁንም ነዪ፥ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “የራስሽንና የልጅሽን የሰሎሞንን ሕይወት ለማትረፍ እንድትችይ ልምከርሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሁንም ነዪ፤ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኝ እመክርሻለሁ።

参见章节 复制




1 ነገሥት 1:12
14 交叉引用  

ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”


ሄደሽ ወደ ንጉሡ ወደ ዳዊት ግቢና፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ አል​ማ​ል​ህ​ል​ኝ​ምን? ስለ​ም​ንስ አዶ​ን​ያስ ይነ​ግ​ሣል? በዪው።


ይህ ባይ​ሆን፥ ጌታዬ ንጉሥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎ​ሞን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ቈ​ጠ​ራ​ለን።”


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የይ​ሁ​ዳን ቤተ መን​ግ​ሥት ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።


ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።


ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።


ኤር​ም​ያ​ስም ንጉ​ሡን ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “ብነ​ግ​ርህ በውኑ አት​ገ​ድ​ለ​ኝ​ምን? ብመ​ክ​ር​ህም አት​ሰ​ማ​ኝም” አለው።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።


ጳው​ሎ​ስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለ​ቃ​ውና ለወ​ታ​ደ​ሮቹ፥ “እነ​ዚህ ቀዛ​ፊ​ዎች በመ​ር​ከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አት​ች​ሉም” አላ​ቸው።


ወደ አባ​ቱም ቤት ወደ ኤፍ​ራታ ገባ፤ ሰባ የሆ​ኑ​ትን የይ​ሩ​በ​ኣ​ልን ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ንድ ድን​ጋይ ላይ ገደ​ላ​ቸው፤ ትንሹ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ ኢዮ​አ​ታም ግን ተሸ​ሽጎ ነበ​ርና ተረፈ።


跟着我们:

广告


广告