Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንግዲህ፣ ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ ስለ መብላት፣ በዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት በዓለም ከንቱ እንደ ሆነና ከአንዱ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት የሆነ እንደ ሆነ ጣዖት ሕይወት የሌለው እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 8:4
33 交叉引用  

“አቤቱ፥ በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል።


እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”


እና​ንተ ከየት ናችሁ? ከየ​ትስ ሠሯ​ችሁ? ከም​ድር የሚ​መ​ር​ጧ​ች​ሁም የረ​ከሱ አይ​ደ​ሉ​ምን?


ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ ነው፤ እር​ሱም ሕያው አም​ላ​ክና የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ ነው፤ ከቍ​ጣው የተ​ነሣ ምድር ትን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣ​ለች፤ አሕ​ዛ​ብም መዓ​ቱን አይ​ች​ሉም።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው “ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ ‘እስራኤል ሆይ! ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፤


እን​ዲ​ህም አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እኛስ እንደ እና​ንተ የም​ን​ሞት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታ​ችሁ ሰማ​ይና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ያለ​ውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ለሱ ዘንድ ወን​ጌ​ልን እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን።


ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው።


አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።


ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል።


አንተ አማኙ በጣ​ዖት ቤት በማ​ዕድ ተቀ​ም​ጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲ​ያው ለጣ​ዖት የተ​ሠ​ዋ​ውን ደፍሮ ይበ​ላል።


ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ደካማ ወን​ድም አን​ተን በማ​የት ይጎ​ዳል።


ነገር ግን ቀድሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባለ​ማ​ወ​ቃ​ችሁ፥ በባ​ሕ​ር​ያ​ቸው አማ​ል​ክት ላል​ሆኑ ተገ​ዝ​ታ​ችሁ ነበር።


በሁሉ ሙሉ የሚ​ሆን ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ገኘ ከሁ​ሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ ነው።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ታላ​ቅ​ነ​ት​ህ​ንና ኀይ​ል​ህን፥ የጸ​ናች እጅ​ህ​ንና የተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድ​ህን ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ማሳ​የት ጀም​ረ​ሃል፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድ​ርም እንደ ሥራህ፥ እንደ ኀይ​ል​ህም ይሠራ ዘንድ የሚ​ችል አም​ላክ ማን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ አድ​ን​ማ​ለሁ፤ እኔ እገ​ር​ፋ​ለሁ፤ ይቅ​ርም እላ​ለሁ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አም​ላክ እንደ ሆነና ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ እን​ድ​ታ​ውቅ፥


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤


ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።


አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告