1 ቆሮንቶስ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አንተ አማኙ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲያው ለጣዖት የተሠዋውን ደፍሮ ይበላል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 አንተ ይህን የመሰለ ዕውቀት ኖሮህ፣ ደካማ ኅሊና ያለው ሰው በቤተ ጣዖት ስትበላ ቢያይህ፣ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ ለመብላት አይደፋፈርምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይደፋፈርምን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “ዕውቀት አለኝ” ብለህ ለጣዖት የተሠዋውን በቤተ ጣዖት ስትበላ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ቢያይህ ይህ ድርጊትህ ሰውየው ለጣዖት የተሠዋውን እንዲበላ ያደፋፍረው የለምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን? 参见章节 |