Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 7:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ የታ​ሠ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወ​ደ​ደ​ች​ውን ታግባ፤ ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከርሱ ጋራ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ሚስት ባሏ በሕይወት እስካለ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ሚስት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ በጋብቻ ሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን የፈለገችውን ለማግባት ነጻ ነች፤ ሆኖም የምታገባው ሰው ክርስቲያን መሆን አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 7:39
8 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


እግዚአብሔር የወደደውን መቅደስ ይሁዳ አርክሶአልና፥ የእንግዳውንም አምላክ ልጅ ሚስት አድርጎ አግብቶአልና ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኵሰት ተሠርቶአል።


ያገ​ቡ​ት​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ አዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በራሴ ትእ​ዛ​ዝም አይ​ደ​ለም፤ ሚስ​ትም ከባ​ልዋ አት​ፋታ።


የማ​ያ​ምን ግን ቢፈታ ይፍታ፤ ወን​ድ​ምና እኅት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰ​ላም ስለ ጠራ​ቸው እን​ደ​ዚህ ላለ ግብር አይ​ገ​ዙ​ምና።


ድን​ግ​ሊ​ቱን ያገባ መል​ካም አደ​ረገ፤ ያላ​ገባ ግን የም​ት​ሻ​ለ​ውን አደ​ረገ።


跟着我们:

广告


广告