Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 7:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ወንድሞች ሆይ፤ ሐሳቤ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ ዐጭር ነው፤ ከእንግዲህ ሚስት ያላቸው እንደሌላቸው ሆነው ይኑሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ዳሩ ግን ወንድሞች ሆይ! ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ወንድሞች ሆይ! እኔ የምላችሁ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ አጥሮአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለችው ሆኖ ይኑሩ። ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌሉአቸው ሆነው ይኑር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 7:29
23 交叉引用  

ቤር​ዜ​ሊም ንጉ​ሡን አለው፥ “ከን​ጉሡ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እወጣ ዘንድ ከሕ​ይ​ወቴ ዘመን ምን ያህል ቀረኝ?


ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ጊዜው መጥ​ቶ​አል፤ ቀኑ እነሆ ቀር​ቦ​አል፤ መቅ​ሠ​ፍቷ በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ መል​ቶ​አ​ልና የሚ​ገዛ ደስ አይ​በ​ለው፤ የሚ​ሸ​ጥም አይ​ዘን።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።


ብታ​ገ​ባም ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ብ​ህም፤ ድን​ግ​ሊ​ቱም ባል ብታ​ገባ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ትም፤ ያገቡ ግን ለራ​ሳ​ቸው ድካ​ምን ይሻሉ፤ እኔም ይህን የም​ላ​ችሁ ስለ​ማ​ዝ​ን​ላ​ችሁ ነው።


ያለ​ቀሱ እን​ዳ​ላ​ለ​ቀሱ ይሆ​ናሉ፤ ደስ ያላ​ቸ​ውም ደስ እን​ዳ​ላ​ላ​ቸው ይሆ​ናሉ፤ የሸ​ጡም እን​ዳ​ል​ሸጡ ይሆ​ናሉ፤ የገ​ዙም እን​ዳ​ል​ገዙ ይሆ​ናሉ።


የበሉ እን​ዳ​ል​በሉ ይሆ​ናሉ፤ የጠ​ጡም እን​ዳ​ል​ጠጡ ይሆ​ናሉ፤ የዚህ ዓለም ተድላ ሁሉ ያል​ፋ​ልና።


“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ፤


ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።


跟着我们:

广告


广告