Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ማን ይመ​ረ​ም​ር​ሃል? የም​ት​ታ​በ​ይስ በም​ን​ድን ነው? ከሌላ ያላ​ገ​ኘ​ኸው አለ​ህን? ያለ​ህ​ንም ከሌላ ካገ​ኘህ እን​ዳ​ላ​ገኘ ለምን ትኮ​ራ​ለህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለመሆኑ፣ አንተን ከሌላው እንድትበልጥ ያደረገህ ማን ነው? ያልተቀበልኸው የራስህ የሆነ ነገር ምን አለ? ከተቀበልህ ታዲያ፣ እንዳልተቀበልህ ለምን ትመካለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አንተን እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? እንግዲህ የተቀበልክ ከሆንክ፥ እንዳልተቀበልክ የምትመካው ስለ ምንድነው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው?

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 4:7
29 交叉引用  

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በወ​ን​ዞች መካ​ከል የሚ​ተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራ​ሴም ሠር​ቼ​ዋ​ለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ሆይ! እነሆ በአ​ንተ ላይ ነኝ።


ዐሥ​ሩን አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣ​ቸ​ውና፦ እን​ግ​ዲህ እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ነግዱ አላ​ቸው።


እኛም ሁላ​ችን ከሙ​ላቱ በጸጋ ላይ ጸጋን ተቀ​በ​ልን።


ዮሐ​ን​ስም መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ሰው ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠው በስ​ተ​ቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገን​ዘብ ሊያ​ደ​ርግ ምንም አይ​ች​ልም።


በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥


በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠን ጸጋ መጠን ልዩ ልዩ ስጦታ አለን። ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እንደ እም​ነቱ መጠን ይና​ገር።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለ​ሁ​በት አለሁ፤ ለእ​ኔም የሰ​ጠኝ ጸጋው ለከ​ንቱ የሆ​ነ​ብኝ አይ​ደ​ለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከ​ምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አጸ​ናኝ እንጂ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁም።


እን​ግ​ዲህ ጳው​ሎስ ምን​ድን ነው? አጵ​ሎ​ስስ ምን​ድን ነው? እነ​ር​ሱስ በቃ​ላ​ቸው የአ​መ​ና​ችሁ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ነው።


እን​ግ​ዲ​ያስ መታ​በ​ያ​ችሁ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጥቂቱ እርሾ ብዙ​ውን ሊጥ እን​ደ​ሚ​ያ​መጥ አታ​ው​ቁ​ምን?


ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወ​ዳ​ለ​ሁና፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ጸጋ ይኑር፤ ግብሩ እን​ዲህ የሆነ አለና፤ ግብሩ ሌላ የሆ​ነም አለና።


በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፤ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ፤


跟着我们:

广告


广告