Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እን​ኪ​ያስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ ፈጥኜ እመ​ጣ​ለሁ፤ ነገር ግን የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ነገር አል​ሻም፤ ኀይ​ላ​ቸ​ውን እሻ​ለሁ እንጂ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ ከዚያም እነዚህ ትዕቢተኞች የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን፣ ምን ኀይል እንዳላቸውም ማየት እሻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ የትዕቢተኞችንም ኃይል አውቃለሁ እንጂ ቃላቸውን አይደለም፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይሁን እንጂ የጌታ ፈቃድ ቢሆን በቅርብ ጊዜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ የእነዚህን ትዕቢተኞች ንግግራቸውን ብቻ ሳይሆን ኀይላቸውንም ማወቅ እፈልጋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ፥ የትዕቢተኞችንም ኃይል አውቃለሁ እንጂ ቃላቸውን አይደለም፤

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 4:19
18 交叉引用  

ከዚ​ህም በኋላ በሚ​ሸ​ኙት ጊዜ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቢፈ​ቅድ እን​ደ​ገና እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ አሁን ግን የሚ​መ​ጣ​ውን በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላደ​ርግ እወ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ ከኤ​ፌ​ሶ​ንም በመ​ር​ከብ ሄደ።


ይህም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ በመ​ቄ​ዶ​ን​ያና በአ​ካ​ይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ፥ “እዚ​ያም ከደ​ረ​ስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገ​ባ​ኛል” አለ።


በዚያ አው​ራ​ጃም አልፎ ሄደ፤ በቃ​ሉም ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ግሪክ ሀገር ሄደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ በደ​ስታ ወደ እና​ንተ መጥቼ ከእ​ና​ንተ ጋር ዐርፍ ዘንድ ነው።


መሰ​ብ​ሰ​ባ​ችሁ ለፍዳ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የተ​ራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አት​ነ​ቃ​ቀ​ፉም፤ ሌላ​ውን ሥር​ዐት ግን መጥቼ እሠ​ራ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሁላ​ች​ሁም በቋ​ንቋ ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ሳይ​ተ​ረ​ጕም በቋ​ንቋ ከሚ​ና​ገር ይልቅ ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እጅግ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ቢተ​ረ​ጕም ግን ማኅ​በ​ሩን ያን​ጻል።


መቄ​ዶ​ን​ያም ደርሼ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በመ​ቄ​ዶ​ንያ በኩል አል​ፋ​ለ​ሁና።


አሁን እግረ መን​ገ​ዴን ላያ​ችሁ አል​ሻም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ቀደ እንደ ሆነ የሆ​ነ​ውን ቀን ያህል በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ደ​ም​ቈይ ተስፋ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ለዐ​ዋ​ቆች ጥበ​ብን እን​ነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለን፤ ነገር ግን የዚ​ህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላ​ቸ​ውን የዚ​ህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይ​ደ​ለም።


እነሆ፥ ወደ እና​ንተ ስላ​ል​መ​ጣሁ ከእ​ና​ንተ ወገን የታ​በዩ ሰዎች አሉ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ! እኔም፥ አጵ​ሎ​ስም ብን​ሆን መከራ የተ​ቀ​በ​ል​ነው ስለ እና​ንተ ነው፤ እና​ንተ እን​ድ​ት​ማሩ፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልም ወጥ​ታ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዳ​ት​ታ​በዩ ነው።


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን በመ​ል​እ​ክ​ቶች የማ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ችሁ እን​ዳ​ይ​መ​ስ​ላ​ችሁ፥ ይህን ትም​ክ​ሕ​ቴን እተ​ወ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቢፈ​ቅድ ይህን ባደ​ረ​ግን ነበር።


በዚህ ፈንታ “ጌታ ቢፈቅድ፥ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን፤” ማለት ይገባችኋል።


跟着我们:

广告


广告