Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሥራ ይገ​ለ​ጻል፤ እሳ​ትም በፈ​ተ​ነው ጊዜ ቀኑ ይገ​ል​ጠ​ዋል፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱ​ንም ሥራ እሳት ይፈ​ት​ነ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሥራው እንዴት እንደ ሆነ ይታያል፤ ምክንያቱም ያ ቀን ወደ ብርሃን ያመጣዋል። በእሳት ስለሚገለጥ እሳቱ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ምንነት ይፈትናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ፥ ያ ቀን በገሃድ ያሳያልና፤ የእያንዳንዱም ሥራ ምን መሆኑን እሳቱ ራሱ ይፈትነዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የእያንዳንዱ ሰው ሥራ የሚገለጥበት የፍርድ ቀን ይመጣል፤ በዚያን ቀን የእያንዳንዱ ሰው ሥራ ምን ዐይነት እንደ ሆነ በእሳት ተፈትኖ ይገለጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 3:13
28 交叉引用  

ፍር​ዴን ለተ​ስፋ ይቅ​ር​ታ​ዬ​ንም ለት​ክ​ክ​ለኛ ሚዛን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በከ​ን​ቱና በሐ​ሰት የሚ​ታ​መኑ ከዐ​ውሎ ነፋስ አያ​መ​ል​ጡም።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በውኑ ቃሌ እንደ እሳት፥ ድን​ጋ​ዩ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ቅቅ መዶሻ አይ​ደ​ለ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።


ነገር ግን እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና የሚመጣበትን ቀን መታገሥ የሚችል ማን ነው? እርሱስ በተገለጠ ጊዜ የሚቆም ማን ነው?


እውነት እላችኋለሁ፤ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


ባንቺ ግን በል​ብሽ ፍላጻ ይገ​ባል፤ የብ​ዙ​ዎ​ቹን ዐሳብ ይገ​ልጥ ዘንድ።”


ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እኔ በወ​ን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ ሰዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው የሰ​ወ​ሩ​ት​ንና የሸ​ሸ​ጉ​ትን በሚ​መ​ረ​ም​ር​በት ጊዜ የሚ​ና​ገ​ሩ​ትና የሚ​መ​ል​ሱት እን​ደ​ሌለ ስለ​ሚ​ያ​ውቁ ነው።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


እር​ሱም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸ​ና​ች​ኋል።


በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ስለዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ ተቀብዬአለሁ፤ ነገር ግን አላፍርበትም፤ ያመንሁትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንዲችል ተረድቼአለሁ።


በዚያን ቀን ከጌታ ምሕረትን እንዲያገኝ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ።


ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።


ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።


ሌሎች ልማድ አድ​ር​ገው እንደ ያዙት ማኅ​በ​ራ​ች​ንን አን​ተው፤ እርስ በር​ሳ​ችን እን​መ​ካ​ከር እንጂ፤ ይል​ቁ​ንም ቀኑ ሲቀ​ርብ እያ​ያ​ችሁ አብ​ል​ጣ​ችሁ ይህን አድ​ርጉ።


ወዳጆች ሆይ! በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደ መጣባችሁ አትደነቁ፤


የጌታው ቀን ግን እንደ ሌባ ሆኖ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይቀልጣል፤ ምድርም በእርስዋም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።


አሁን ያሉ ሰማያትና ምድር ግን እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ተጠብቀው በዚያ ቃል ለእሳት ቀርተዋል።


ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።


跟着我们:

广告


广告