Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔም ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ በማ​ባ​በ​ልና ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትም​ህ​ርት ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ምስጢር በረቀቀ የንግግር ችሎታ ወይም በላቀ ጥበብ ልገልጥላችሁ አልመጣሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወንድሞች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ የእግዚአብሔርን ምስጢር በቃላት መራቀቅ ወይም ጥበብ ለእናንተ ለማወጅ አልመጣሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር የመሰከርኩት የንግግርን ችሎታና የፍልስፍናን ጥበብ በማሳየት አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 2:1
23 交叉引用  

ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።”


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤


‘ስለ እኔ የም​ት​መ​ሰ​ክ​ረ​ውን ምስ​ክ​ር​ነት አይ​ቀ​በ​ሉ​ህ​ምና ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፈጥ​ነህ ውጣ’ ሲለኝ አየ​ሁት።


እነ​ርሱ ለጌ​ታ​ችን ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያይ​ደለ ለሆ​ዳ​ቸው ይገ​ዛ​ሉና፤ በነ​ገር ማታ​ለ​ልና በማ​ለ​ዛ​ዘ​ብም የብ​ዙ​ዎች የዋ​ሃ​ንን ልብ ያስ​ታሉ፤


ይህም በነ​ቢ​ያት ቃልና የዘ​ለ​ዓ​ለም ገዥ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ በዚህ ወራት ተገ​ለጠ፤ አሕ​ዛብ ሁሉ ይህን ሰም​ተ​ውና ዐው​ቀው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያምኑ ዘንድ።


ክር​ስ​ቶስ ወን​ጌ​ልን ለመ​ስ​በክ እንጂ ለማ​ጥ​መቅ አል​ላ​ከ​ኝ​ምና፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀ​ሉን ከንቱ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለም።


ለክ​ር​ስ​ቶስ መመ​ስ​ከሬ በእ​ና​ንተ እንደ ጸና መጠን።


ይህም ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከሰው የተ​ገኘ ትም​ህ​ርት አይ​ደ​ለም፤ የአ​ነ​ጋ​ገር ጥበ​ብም አይ​ደ​ለም፤ መን​ፈስ ቅዱስ የገ​ለ​ጸው ትም​ህ​ርት ነው እንጂ፤ መን​ፈ​ሳዊ ጥበ​ብም ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ሆ​ነ​ውን መር​ም​ረው ለሚ​ያ​ውቁ ለመ​ን​ፈ​ሳ​ው​ያን ነው።


ቃሌም፥ ትም​ህ​ር​ቴም መን​ፈ​ስ​ንና ኀይ​ልን በመ​ግ​ለጥ ነበር እንጂ በሚ​ያ​ባ​ብል በጥ​በብ ቃል አል​ነ​በ​ረም።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ከዘ​መ​ናት በፊት ለክ​ብ​ራ​ችን የወ​ሰ​ነ​ውን ተሰ​ው​ሮም የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በም​ሥ​ጢር እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።


እኔ በአ​ነ​ጋ​ገሬ አላ​ዋቂ ብሆ​ንም በዕ​ው​ቀት ግን እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኀይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤


እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።


እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።


እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告