Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 16:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በእ​ስያ ያሉ ምእ​መ​ናን ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል፤ አቂ​ላና ጵር​ስ​ቅላ በቤ​ታ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር ያሉ ምእ​መ​ና​ንም ሁሉ በጌ​ታ​ችን እጅግ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፥ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያን ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ አቂላና ጵርስቅላ፥ በቤታቸው የሚሰበሰቡ ክርስቲያኖችም ሁሉ ልባዊ ሰላምታ በጌታ ስም ያቀርቡላችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእስያ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ በቤታቸው ካለች ቤተ ክርስቲያን ጋር በጌታ እጅግ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 16:19
13 交叉引用  

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤


ጳው​ሎ​ስም እንደ ገና በወ​ን​ድ​ሞቹ ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀ​መጠ፤ በሰ​ላ​ምም ሸኙ​ትና ወደ ሶርያ በባ​ሕር ተጓዘ፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም አብ​ረ​ውት ነበሩ፤ ስእ​ለ​ትም ነበ​ረ​በ​ትና በክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ራሱን ተላጨ።


አቂላ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳ​ዊም አገኘ፤ የት​ው​ልድ ሀገ​ሩም ጳን​ጦስ ነው፤ እር​ሱም ከጥ​ቂት ወራት በፊት ከኢ​ጣ​ልያ ተሰዶ መጣ፤ ሚስቱ ጵር​ስ​ቅ​ላም አብ​ራው ነበ​ረች፤ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ አይ​ሁድ ከሮም እን​ዲ​ሰ​ደዱ አዝዞ ነበ​ርና ወደ እነ​ርሱ መጣ።


እር​ሱም በም​ኵ​ራብ በግ​ልጥ ይና​ገር ጀመር፤ ጵር​ስ​ቅ​ላና አቂ​ላም በሰ​ሙት ጊዜ ወደ ማደ​ሪ​ያ​ቸው ወስ​ደው ፍጹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ አስ​ረ​ዱት።


በእ​ስ​ያም ያሉ አይ​ሁ​ድና አረ​ማ​ው​ያን ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እስ​ኪ​ሰሙ ድረስ እን​ደ​ዚሁ ሁለት ዓመት ኖረ።


እኛ በተ​ወ​ለ​ድ​ን​በት በጳ​ርቴ፥ በሜድ፥ በኢ​ላ​ሜጤ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል፥ በይ​ሁዳ፥ በቀ​ጰ​ዶ​ቅያ፥ በጳ​ን​ጦ​ስና በእ​ስያ፥


ፊሎ​ሎ​ጎ​ስን፥ ዩል​ያን፥ ኔር​ዮ​ስን፥ እኅ​ቱ​ንም አሊ​ን​ጳ​ስን ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያሉ ቅዱ​ሳ​ንን ሁሉ ሰላም በሉ።


በሎ​ዶ​ቅያ ላሉት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና ለን​ም​ፋን፥ በቤ​ቱም ላለች ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ አቅ​ር​ቡ​ልኝ።


ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩም ቤተ ሰዎች ሰላምታ አቅርብልኝ።


ለእኅታችንም ለአፍብያ፥ ከእኛም ጋር አብሮ ወታደር ለሆነ ለአርክጳ፥ በቤትህም ላለች ቤተ ክርስቲያን፤


የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው በመንፈስም እንደሚቀደሱ፥ ይታዘዙና በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ይረጩ ዘንድ ለተመረጡት በጳንጦስና በገላትያ በቀጰዶቅያም በእስያም በቢታንያም ለተበተኑ መጻተኞች፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።


跟着我们:

广告


广告