1 ቆሮንቶስ 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ነፍስ የሌለው ድምፅ የሚሰጥ እንደ መሰንቆ፥ ወይም እንደ ክራር ያለ መሣሪያ በስልት ካልተመታ መሰንቆው ወይም ክራሩ የሚለውን ማን ያውቃል? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 እንደ ዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው ነገሮች እንኳ፣ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው የዋሽንት ወይም የበገና ድምፅ መሆኑን እንዴት ማወቅ ይቻላል? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እንደዋሽንትና እንደ በገና ያሉ ሕይወት የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የድምፃቸው ቃና ልዩነት ከሌለው ዜማቸውን እንዴት ማወቅ ይቻላል? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እንደ ዋሽንትና እንደ ክራር ያሉት ነፍስ የሌላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች እንኳ የተለየ የድምፅ ቅኝት ከሌላቸው የሚሰጡት የሙዚቃ ድምፅ ምን መሆኑ እንዴት ይታወቃል? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ነፍስ የሌለበት ነገር እንኳ ዋሽንትም ክራርም ቢሆን ድምፅ ሲሰጥ የድምፁን ልዩነት ባይገልጥ በዋሽንት የሚነፋው ወይስ በክራር የሚመታው መዝሙር እንዴት ይታወቃል? 参见章节 |