Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 14:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ሁላ​ችሁ በም​ት​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ጊዜ መዝ​ሙር አላ​ችሁ፤ ትም​ህ​ርት አላ​ችሁ፤ መግ​ለጥ አላ​ችሁ፤ በቋ​ንቋ መና​ገር አላ​ችሁ፤ መተ​ር​ጐ​ምም አላ​ችሁ፤ ሁሉም ለሚ​ታ​ነ​ጽ​በት ጥቅም አድ​ር​ጉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ምንድር ነው? በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ መዝሙር አለው፥ ትምህርት አለው፥ መግለጥ አለው፥ በልሳን መናገር አለው፥ መተርጐም አለው፤ ሁሉ ለማነጽ ይሁን።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 14:26
18 交叉引用  

ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ልም በማ​ገ​ል​ገሉ ይትጋ፤ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ርም በማ​ስ​ተ​ማሩ ይትጋ፤


አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።


ሁላ​ች​ንም በእ​ው​ነ​ትና በመ​ል​ካም ሥራ ይታ​ነጽ ዘንድ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችን እና​ድላ።


እን​ግ​ዲህ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ በመ​ን​ፈስ እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈሴ እዘ​ም​ራ​ለሁ፤ በማ​ስ​ተ​ዋ​ልም እዘ​ም​ራ​ለሁ።


በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው የሚ​ና​ገር አይ​ደ​ለም። የሚ​ና​ገ​ረ​ውን የሚ​ሰ​ማው የለ​ምና፥ ነገር ግን በመ​ን​ፈስ ምሥ​ጢ​ርን ይና​ገ​ራል።


በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ቢኖር ሁለት ሁለት፥ ወይም ቢበዛ ሦስት ሦስት እየ​ሆኑ በተራ ይና​ገሩ፤ ሌላ​ውም ይተ​ር​ጕ​ም​ለት።


ነገር ግን ሁሉን በአ​ገ​ባ​ብና በሥ​ር​ዐት አድ​ርጉ፤


እኛስ ደግሞ ስለ ራሳ​ችን የም​ን​ከ​ራ​ከ​ራ​ችሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ ሆነን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህ ሁሉ ግን እና​ንተ ትታ​ነጹ ዘንድ ነው።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።


ቅዱ​ሳን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሥራና ለክ​ር​ስ​ቶስ አካል ሕንጻ እን​ዲ​ጸኑ፤


ከእ​ርሱ የተ​ነሣ አካል ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ክፍል በልክ እን​ደ​ሚ​ሠራ፥ በተ​ሰ​ጠው በሥር ሁሉ እየ​ተ​ጋ​ጠ​መና እየ​ተ​ያ​ያዘ፥ ራሱን በፍ​ቅር ለማ​ነጽ አካ​ሉን ያሳ​ድ​ጋል።


የሚ​ሰ​ሙ​አ​ችሁ ሞገ​ስን ያገኙ ዘንድ፥ ግዳ​ጃ​ችሁ እን​ዲ​ፈ​ጸም መል​ካም ነገር እንጂ ክፉ ነገር ሁሉ ከአ​ፋ​ችሁ አይ​ውጣ።


መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የተ​ቀ​ደሰ ማሕ​ሌ​ት​ንም አን​ብቡ፤ በል​ባ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀኙ፤ ዘም​ሩም።


ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።


跟着我们:

广告


广告