Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ቆሮንቶስ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የሰ​ውን ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ የመ​ላ​እ​ክ​ት​ንም ሁሉ ቋንቋ ባውቅ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ እን​ደ​ሚ​ጮህ ነሐስ፥ ወይም እን​ደ​ሚ​መታ ከበሮ መሆኔ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በሰዎችም ሆነ በመላእክት ቋንቋ የመናገር ችሎታ ቢኖረኝ እንኳ ፍቅር ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል መሆኔ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

参见章节 复制




1 ቆሮንቶስ 13:1
22 交叉引用  

ድምፁ መል​ካም በሆነ ጸና​ጽል አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በጸ​ና​ጽ​ልና በእ​ል​ልታ አመ​ስ​ግ​ኑት።


ያን ጊዜ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም፤’ ብሎ ይመልስላቸዋል።


ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤


በመ​ብል ምክ​ን​ያት ባል​ን​ጀ​ራ​ህን የም​ታ​ሳ​ዝን ከሆ​ንህ ፍቅር የለ​ህም፤ በውኑ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ የሞ​ተ​ለት ያ ሰው በመ​ብል ምክ​ን​ያት ሊጐዳ ይገ​ባ​ልን?


ለአ​ን​ዱም ተአ​ም​ራ​ትን ማድ​ረግ፥ ለአ​ን​ዱም ትን​ቢ​ትን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም መና​ፍ​ስ​ትን መለ​የት፥ ለአ​ን​ዱም በልዩ ዓይ​ነት ልሳን መና​ገር፥ ለአ​ን​ዱም በል​ሳ​ኖች የተ​ነ​ገ​ረ​ውን መተ​ር​ጐም ይሰ​ጠ​ዋል።


ጆሮም፥ “እኔ ዐይን አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና የአ​ካል ክፍል አይ​ደ​ለ​ሁም” ብትል ይህን በማ​ለቷ የአ​ካል ክፍል መሆ​ንዋ ይቀ​ራ​ልን?


በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጥ​በብ ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የዕ​ው​ቀት ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ።


ፍቅር ለዘ​ወ​ትር አይ​ጥ​ልም፤ ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይሻ​ራ​ልም፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚ​ና​ገ​ርም ያል​ፋል፤ ይቀ​ራል፤ የሚ​ራ​ቀ​ቅም ያል​ፋል፤ ይጠ​ፋል።


በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ ለሰው የሚ​ና​ገር አይ​ደ​ለም። የሚ​ና​ገ​ረ​ውን የሚ​ሰ​ማው የለ​ምና፥ ነገር ግን በመ​ን​ፈስ ምሥ​ጢ​ርን ይና​ገ​ራል።


በቋ​ንቋ የሚ​ና​ገር ራሱን ያን​ጻል፤ የሚ​ተ​ረ​ጕም ግን የክ​ር​ስ​ቲ​ያን ማኅ​በ​ርን ያን​ጻል።


ሁላ​ች​ሁም በቋ​ንቋ ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ እወ​ዳ​ለሁ፤ ሳይ​ተ​ረ​ጕም በቋ​ንቋ ከሚ​ና​ገር ይልቅ ትን​ቢት የሚ​ና​ገር እጅግ ይበ​ል​ጣ​ልና፤ ቢተ​ረ​ጕም ግን ማኅ​በ​ሩን ያን​ጻል።


ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል።


ወደ ገነ​ትም ነጥ​ቀው ወሰ​ዱት፤ በዚ​ያም ሰው ሊና​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለ​ውን የማ​ይ​ተ​ረ​ጐም ነገር ሰማ።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና።


የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤


ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኀጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፤ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።


እንደ ብዙ ውሃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ፤ ደርዳሪዎችም በገና እንደሚደረድሩ ያለ ድምፅ ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告