Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ያግ​ቤ​ጽም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ይልቅ የተ​ከ​በረ ነበረ፤ እና​ቱም፦ በጣር ወል​ጄ​ዋ​ለ​ሁና ብላ ስሙን፦ ያግ​ቤጽ ብላ ጠራ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ያቤጽ ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ሰው ነበረ፤ እናቱም “በጣር የወለድሁት” ስትል ስሙን ያቤጽ አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከቤተሰቡ መካከል እጅግ የተከበረ ያዕቤጽ ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እናቱ እርሱን በወለደች ጊዜ ከባድ የምጥ ጣር ደርሶባት ስለ ነበር “ያዕቤጽ” የሚል ስም አወጣችለት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን “ያቤጽ” ብላ ጠራችው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 4:9
10 交叉引用  

ለሴ​ቲ​ቱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላት፥ “ጭን​ቅ​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፤ በጭ​ንቅ ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ከወ​ለ​ድ​ሽም በኋላ ፈቃ​ድሽ ወደ ባልሽ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም ይገ​ዛ​ሻል።”


ብላ​ቴ​ና​ውም ይህን ነገር ያደ​ርግ ዘንድ አል​ዘ​ገ​የም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ ወድ​ዶ​አ​ልና፤ እር​ሱም ከአ​ባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከ​በረ ነበረ።


ከዚ​ያም በኋላ ነፍ​ስዋ ልት​ወጣ ደረ​ሰች፤ ሞትዋ በእ​ርሱ ሆኖ​አ​ልና ስሙን የጭ​ን​ቀቴ ልጅ ብላ ጠራ​ችው ፤ አባቱ ግን ብን​ያም አለው።


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


ቆስ፥ ኢኖ​ብን፥ ሲባ​ባን፥ የሃ​ሩ​ም​ንም ልጅ የሬ​ካ​ብን ወን​ድም ወገ​ኖች ወለደ።


ወደ ሚስ​ቱም ገባ፥ አረ​ገ​ዘ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ በቤ​ቴም መከራ ሆኖ​አ​ልና ሲል ስሙን በሪዓ ብሎ ጠራው።


አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይላቸዋል፥ አንተንም የወለደች ደስ ይላታል።


በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ።


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


እር​ስ​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ተማ​ረ​ከች፥ ስለ አማ​ቷና ስለ ባል​ዋም፦ የሕ​ፃ​ኑን ስም ዊቦ​ር​ኮ​ኢ​ቦት ብላ ጠራ​ችው።


跟着我们:

广告


广告