Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 29:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በነ​ጋ​ውም ዳዊት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረበ፤ አንድ ሺህ ወይ​ፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦ​ቶች፥ የመ​ጠጥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ው​ንም፥ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ብዙ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በማግስቱም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሠዉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም አቀረቡ፤ ይህም አንድ ሺሕ ወይፈን፣ አንድ ሺሕ አውራ በግ፣ አንድ ሺሕ የበግ ጠቦት ሲሆን፣ ከመጠጥ ቍርባኖቻቸውና ከሌሎች መሥዋዕቶች ጋራ ስለ እስራኤል ሁሉ በብዛት አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በማግስቱም ለጌታ መሥዋዕት ሰዉ፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቁርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በማግስቱ ብዙ እንስሶችን ዐርደው ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡ እንዲመገቡ ሰጡአቸው፤ በተጨማሪም አንድ ሺህ ኰርማዎችን፥ አንድ ሺህ የበግ አውራዎችንና አንድ ሺህ የበግ ጥቦቶችን መሥዋዕት አድርገው በማረድ ሙሉ በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠሉአቸው፤ የወይን ጠጅ መባም አቀረቡ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በነጋውም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሰዉ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቍርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 29:21
7 交叉引用  

በዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መቶ ወይ​ፈ​ኖ​ችና ሁለት መቶ አውራ በጎች፥ አራት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች አቀ​ረቡ፤ ስለ ኀጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ቍጥር ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት አውራ ፍየ​ሎች አቀ​ረቡ።


የስ​ን​ዴም ቍር​ባን ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ይሁን፤ የመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን የወ​ይን ጠጅ የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ ይሁን።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በእ​ሳት ለተ​ደ​ረገ ቍር​ባን፥ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ግማሽ ወይን ለመ​ጠጥ ቍር​ባን ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም የኢን መስ​ፈ​ሪያ የሆነ መል​ካም ዱቄት አራ​ተኛ እጅ በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ወይም በእ​ህሉ ቍር​ባን ላይ ያደ​ር​ጋል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥ​ዋ​ዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድ​ርግ።


ለመ​ጠጥ ቍር​ባ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሦስ​ተኛ እጅ ወይን ታቀ​ር​ባ​ለህ።


跟着我们:

广告


广告