Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 29:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔም እንደ ጉል​በቴ ሁሉ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወር​ቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረ​ትን፥ እን​ጨ​ትን፥ ደግ​ሞም መረ​ግ​ድ​ንና በፈ​ርጥ የሚ​ገባ ድን​ጋ​ይን፥ የሚ​ለ​ጠፍ ድን​ጋ​ይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለ​ው​ንም ድን​ጋይ፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም ድን​ጋይ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔም ያለኝን ሀብት ለአምላኬ ቤተ መቅደስ ለወርቁ ሥራ ወርቁን፣ ለብሩ ሥራ ብሩን፣ ለናሱ ሥራ ናሱን፣ ለብረቱ ሥራ ብረቱን፣ ለዕንጨቱ ሥራ ዕንጨቱን እንዲሁም ለፈርጥ የሚሆነውን መረግድ፣ ኬልቄዶን፣ ልዩ ልዩ ኅብር ያላቸውን የከበሩ ድንጋዮች፣ ማንኛውንም ዐይነት የሚያምር ድንጋይና ዕብነበረድ፣ ይህን ሁሉ በብዛት አዘጋጅቻለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔም እንደ ጉልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዓይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምችለውን ያኽል፥ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ የሚሆኑትን ዕቃዎች ወርቅ ለወርቅ ሥራ፥ ብር ለብር ሥራ፥ ነሐስ ለነሐስ ሥራ፥ ብረት ለብረት ሥራ፥ እንጨት ለእንጨት ሥራ መርግድና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው በፈርጥ የሚገቡ ድንጋዮች፥ የከበረ ድንጋይና በየዐይነቱ ብዙ ዕብነ በረድ አዘጋጅቼአለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔም እንደ ጕልበቴ ሁሉ ለአምላኬ ቤት ለወርቁ ዕቃ ወርቁን፥ ለብሩም ዕቃ ብሩን፥ ለናሱም ዕቃ ናሱን፥ ለብረቱም ዕቃ ብረቱን፥ ለእንጨቱም ዕቃ እንጨቱን፥ ደግሞ መረግድንና በፈርጥ የሚገባ ድንጋይን፥ የሚለጠፍ ድንጋይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለውንም ድንጋይ፥ የከበረውንም ድንጋይ ከየዐይነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘጋጅቻለሁ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 29:2
22 交叉引用  

የዚ​ያ​ችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው።


ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም ያደ​ርግ ዘንድ፥ ምስ​ክ​ር​ህ​ንም፥ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም ይጠ​ብቅ ዘንድ፥ ያዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ለ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ ለልጄ ለሰ​ሎ​ሞን ቅን ልብን ስጠው።”


ከዚ​ህም በላይ ደግሞ የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ስለ ወደ​ድሁ፥ ለመ​ቅ​ደሱ ከሰ​በ​ሰ​ብ​ሁት ሁሉ ሌላ የግል ገን​ዘቤ የሚ​ሆን ወር​ቅና ብር አለ​ኝና እነሆ፥ ለአ​ም​ላኬ ቤት ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።


ቤቱ​ንም በከ​በ​ረና በተ​መ​ረጠ ዕንቍ፥ በወ​ር​ቅም አስ​ጌ​ጠው፤ ወር​ቁም የፋ​ሩ​ሔም ወርቅ ነበረ።


“በእ​ው​ነቱ ብር የሚ​ወ​ጣ​በት ቦታ አለ፥ ወር​ቅም የሚ​ነ​ጠ​ር​በት ስፍራ አለ።


ከአ​ፌር ወር​ቅም ጋር አት​ወ​ዳ​ደ​ርም። በከ​በረ መረ​ግ​ድና በሰ​ን​ፔር አት​ገ​መ​ትም።


በአ​ራት ተራ የሆነ የዕ​ንቍ ፈርጥ አድ​ር​ግ​በት፤ የድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ተራ ሰር​ድ​ዮን፥ ጳዝ​ዮን፥ መረ​ግድ ነው፤ ይህም መጀ​መ​ሪ​ያው ተራ ነው፤


አራ​ተ​ኛ​ውም ተራ ወር​ቃማ ድን​ጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም በየ​ተ​ራ​ቸው በወ​ርቅ የተ​ለ​በ​ጡና የታ​ሠሩ ይሆ​ናሉ።


ሁለ​ትም የመ​ረ​ግድ ድን​ጋይ ወስ​ደህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስም ስማ​ቸ​ውን ቅረ​ጽ​ባ​ቸው፤


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ተራ ወር​ቃማ ድን​ጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም፤ ዙሪ​ያ​ውም በወ​ርቅ ፈርጥ ተደ​ረገ።


በወ​ርቅ ፈርጥ የተ​ያዙ የመ​ረ​ግድ ድን​ጋ​ዮች ሠር​ተው እንደ ማኅ​ተም ቅርጽ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስም ቀረ​ጹ​ባ​ቸው።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


እነ​ርሱ ሲቻ​ላ​ቸው፥ ሳይ​ቻ​ላ​ቸ​ውም እን​ስጥ በማ​ለት ቈራ​ጦች ለመ​ሆ​ና​ቸው ምስ​ክ​ራ​ቸው እኔ ነኝና።


ለሰው ሳይ​ሆን ለጌታ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ርጉ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ከልብ አድ​ር​ጉት።


跟着我们:

广告


广告