Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ የዘ​ለ​ዓ​ለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአ​ባቴ ቤት ሁሉ መር​ጦ​ኛል፤ ይሁ​ዳ​ንም አለቃ ይሆን ዘንድ መር​ጦ​ታል፤ ከይ​ሁ​ዳም ቤት የአ​ባ​ቴን ቤት መር​ጦ​አል፤ ከአ​ባ​ቴም ልጆች መካ​ከል በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ያነ​ግ​ሠኝ ዘንድ እኔን ሊመ​ር​ጠኝ ወደደ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ለዘላለም እንድነግሥ ከቤተ ሰቤ ሁሉ እኔን መረጠ፤ መሪ እንዲሆንም ይሁዳን መረጠ፤ ከይሁዳም ቤት የእኔን ቤተ ሰብ መረጠ፤ ከአባቴ ልጆች መካከል ደግሞ በመላው እስራኤል ላይ እንድነግሥ ፈቃዱ ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ይሁዳን በእስራኤል ላይ መሪ ነገድ አድርጎ መርጦታል፤ ከይሁዳም የእኔን ቤተሰብ፥ ከእኔም ቤተሰብ እኔን የእስራኤል ንጉሥ እንድሆን መረጠኝ፤ የእኔም ዘሮች ነገሥታት ሆነው እንደሚያስተዳድሩ ቃል ገብቶልኛል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ የዘላለም ንጉሥ እሆን ዘንድ ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ ይሆን ዘንድ መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ያነግሠኝ ዘንድ ሊመርጠኝ ወደደ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 28:4
18 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉሡ ዳዊ​ትም በኬ​ብ​ሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን ቀቡት።


አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ ስለ ባሪ​ያ​ህና ስለ ቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ለዘ​ለ​ዓ​ለም የታ​መነ ይሁን፤ እንደ ተና​ገ​ር​ህም አድ​ርግ።


አሁ​ንም በፊ​ትህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖር ዘንድ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቤት ትባ​ርክ ዘንድ ጀም​ረ​ሃል፤ አን​ተም አቤቱ፥ ባር​ከ​ኸ​ዋል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቡሩክ ይሆ​ናል።”


ይሁ​ዳም በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል በረታ፥ አለ​ቃም ከእ​ርሱ ሆነ፤ በረ​ከት ግን ለዮ​ሴፍ ነበረ።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


ዘመ​ኖ​ቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመ​ቱ​ንም ሌላ ይው​ሰድ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፤ ይቅ​ር​ታ​ው​ንና ጽድ​ቁን ማን ይፈ​ል​ጋል?


ሺህ ዓመት በፊ​ትህ እን​ዳ​ለ​ፈች እንደ ትና​ንት ቀን፥ እንደ ሌሊ​ትም ሰዓት ነውና።


ጌታ​ችን ከይ​ሁዳ ነገድ እንደ ወጣ የተ​ገ​ለጠ ነውና፤ ስለ​ዚ​ህም ነገድ ሙሴ ምንም እን​ኳን ስለ ክህ​ነት አል​ተ​ና​ገ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እን​ዳ​ይ​ነ​ግሥ ለና​ቅ​ሁት ለሳ​ኦል የም​ታ​ለ​ቅ​ስ​ለት እስከ መቼ ነው? የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ሞል​ተህ ና፤ በል​ጆቹ መካ​ከል ለእኔ ንጉሥ አዘ​ጋ​ጅ​ቼ​አ​ለ​ሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እል​ክ​ሃ​ለሁ” አለው።


የዚፍ ሰዎ​ችም ከአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ወደ ኮረ​ብ​ታው ወደ ሳኦል መጥ​ተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየ​ሴ​ሞን ፊት ለፊት ባለው በኤ​ኬላ ኮረ​ብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸ​ሽጎ አለ” አሉት።


跟着我们:

广告


广告