Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 26:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ወን​ድ​ሞ​ቹም ጽኑ​ዓን የነ​በ​ሩት የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉ​ሡም ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሁሉና በን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ በሮ​ቤ​ላ​ው​ያ​ንና በጋ​ዳ​ው​ያን፥ በም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ላይ ሹሞች አደ​ረ​ጋ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ንጉሥ ዳዊት ከእነዚያ ዘመዶች መካከል ምርጥ የሆኑ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ የቤተሰብ አለቆችን መረጠ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ማለትም በሮቤል፥ በጋድና በምናሴ ነገድ እኩሌታ ግዛቶች መንፈሳዊውንና ዓለማዊውን ጉዳይ ሁሉ የማስተዳደር ኀላፊነት ሰጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት ለእግዚአብሔር ጉዳይ ሁሉና ለንጉሡ ጉዳይ በሮቤላውያንና በጋዳውያን በምናሴም ነገድ እኵሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 26:32
7 交叉引用  

በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ካሉ ከሮ​ቤ​ልና ከጋድ ሰዎች ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ንም ሁሉ ይዘው የመጡ መቶ ሃያ ሺህ ነበሩ።


“እና​ንተ የሌ​ዋ​ው​ያን አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ናችሁ፤ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላት ስፍራ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ታመጡ ዘንድ እና​ን​ተና ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​ደሱ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።


እነ​ዚ​ህም ደግሞ በን​ጉሡ በዳ​ዊ​ትና በሳ​ዶቅ በአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም በሌ​ዋ​ው​ያ​ንና በካ​ህ​ናት አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት፥ ታላ​ላ​ቆች እንደ ታና​ናሽ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እንደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አሮን ልጆች ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችና የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም ለን​ጉ​ሡና ለን​ጉሡ ትእ​ዛዝ ሁሉ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ሹማ​ምት እንደ ቍጥ​ራ​ቸው በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው እነ​ዚህ ነበሩ። እነ​ዚ​ህም ክፍ​ሎች እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ሃያ አራት ሺህ ሆነው በዓ​መቱ ወራት ሁሉ በየ​ወሩ ይገ​ቡና ይወጡ ነበር።


እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሆ​ነው ነገር ሁሉ የካ​ህ​ናቱ አለቃ አማ​ርያ፥ በን​ጉ​ሡም ነገር ሁሉ የይ​ሁዳ ቤት አለቃ የይ​ስ​ማ​ኤል ልጅ ዝባ​ድ​ያስ በላ​ያ​ችሁ ተሾ​መ​ዋል፤ ጸሐ​ፍ​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ ደግሞ በፊ​ታ​ችሁ አሉ፤ በር​ት​ታ​ች​ሁም አድ​ርጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ከሚ​ያ​ደ​ርግ ጋር ይሁን።


ኢያ​ሱም ሮቤ​ል​ንና ጋድን የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


跟着我们:

广告


广告