Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 26:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከይ​ሰ​ዓ​ራ​ው​ያን ከና​ን​ያና ልጆቹ ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ይሆኑ ዘንድ በው​ጭው ሥራ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ተሾ​መው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ከይስዓራውያን፤ ከናንያና ወንዶች ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጭ ባለው ሥራ በእስራኤል ላይ ሹማምትና ዳኞች ሆነው ተመደቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች እንዲሆኑ በውጭው በሚከናወነው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከይጽሃር ልጆች መካከል፥ ከናንያና ልጆቹ ከቤተ መቅደሱ ውጪ በመንግሥት ሥራ ሹማምንትና ዳኞች ሆነው ተሹመው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከይስዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ሹማምትና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሹመው ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 26:29
11 交叉引用  

የቀ​ዓት ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፦ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል አራት ነበሩ።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


ከእ​ን​በ​ረ​ማ​ው​ያን፥ ከይ​ስ​ዓ​ራ​ው​ያን፥ ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን፥ ከዑ​ዝ​ኤ​ላ​ው​ያን፤


ነቢዩ ሳሙ​ኤል፥ የቂ​ስም ልጅ ሳኦል፥ የኔ​ርም ልጅ አበ​ኔር፥ የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ ኢዮ​አብ የቀ​ደ​ሱት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንዋየ ቅድ​ሳት ሁሉ ከሰ​ሎ​ሚ​ትና ከወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ በታች ነበረ።


በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር አም​ስ​ተ​ኛው አለቃ ይዝ​ራ​ዊው ሰማ​ኦት ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።


በተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎ​ችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚ​ሠሩ ላይ ተሾ​መው ነበር፤ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹና አለ​ቆ​ቹም በረ​ኞ​ቹም ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን ነበሩ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በውጭ በነ​በ​ረው ሥራ ላይ የነ​በሩ የሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ሴቤ​ታ​ይና ኢዮ​ዛ​ብድ፤


ለቀ​ዓ​ትም የእ​ን​በ​ረም ወገን፥ የይ​ስ​ዓር ወገን፥ የኬ​ብ​ሮ​ንም ወገን፥ የአ​ዛ​ሔ​ልም ወገን ነበሩ፤ የቀ​ዓት ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።


“በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በፍ​ር​ድና በፍ​ርድ መካ​ከል፥ በመ​ቍ​ሰ​ልና በመ​ቍ​ሰል መካ​ከል፥ በክ​ር​ክ​ርና በክ​ር​ክር መካ​ከል በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ሰዎች ስለ​ሚ​ከ​ራ​ከ​ሩ​በት ክር​ክር የሚ​ሳ​ንህ የፍ​ርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነ​ሥ​ተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ መረ​ጠው ስፍራ ትወ​ጣ​ለህ፤


ወደ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት በዚ​ያም ዘመን ወደ አሉ ፈራ​ጆች መጥ​ተህ ትጠ​ይ​ቃ​ለህ፤ እነ​ር​ሱም የፍ​ር​ዱን ነገር ይነ​ግ​ሩ​ሃል።


跟着我们:

广告


广告