Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 26:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ ተሹ​መው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከሌዋውያን መካከል አኪያ የእግዚአብሔር ቤት ግምጃ ቤትና የተቀደሱት ዕቃዎች የሚቀመጡበት ግምጃ ቤት ኀላፊ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅዱሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከሌዋውያን መካከል አኪያ የቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤትና ለእግዚአብሔር መባ ሆነው የሚቀርቡት ዕቃዎች ለሚከማቹባቸው ቤቶች ኀላፊ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅዱሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 26:20
21 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብ​ትና የን​ጉ​ሡን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​ዓ​ዛር ልጆች እጅ ወስዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጣ​ቸ​ውን የወ​ርቅ ጦሮ​ችና ሰሎ​ሞን የሠ​ራ​ቸ​ውን የወ​ር​ቁን ጋሻና ጦር ሁሉ ወደ ግብፅ ወሰደ።


አሳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በን​ጉሥ ቤተ መዛ​ግ​ብት የተ​ገ​ኘ​ውን ብርና ወርቅ ሁሉ ወስዶ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሰጣ​ቸው፤ ንጉ​ሡም አሳ በደ​ማ​ስቆ ለተ​ቀ​መ​ጠው ለአ​ዚን ልጅ ለጤ​ቤ​ር​ማን ልጅ ለሶ​ርያ ንጉሥ ለወ​ልደ አዴር፥


እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የአ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። አባ​ቱም ዳዊት የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ ራሱም የቀ​ደ​ሰ​ውን፥ የብ​ርና የወ​ርቅ ዕቃ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በነ​በሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።


ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።


ከቆ​ሬና ከሜ​ራሪ ልጆች የነ​በሩ የበ​ረ​ኞች ሰሞን ይህች ናት።


የለ​አ​ዳን ልጆች፤ ለለ​አ​ዳን የሆኑ የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ልጆች፥ ለጌ​ድ​ሶ​ና​ዊው ለለ​አ​ዳን የሆኑ፥ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ይሔ​ኤሊ፤


የይ​ሔ​ኤሊ ልጆች፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሚ​ሆኑ ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የነ​በሩ ዜቶም፥ ወን​ድ​ሙም ኢዮ​ኤል ነበረ።


የሙሴ ልጅ የጌ​ር​ሳም ልጅ ሱባ​ኤል በቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ ተሾሞ ነበር።


እነ​ር​ሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝ​ገቡ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አል​ተ​ላ​ለ​ፉም።


ስድሳ አንድ ሺህም የወ​ርቅ ዳሪክ፥ አም​ስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካ​ህ​ናት ልብስ እንደ ችሎ​ታ​ቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛ​ግ​ብት አቀ​ረቡ።


እኔም “እና​ንተ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​ድ​ሳ​ች​ኋል፤ ዕቃ​ዎ​ቹም ቅዱ​ሳን ናቸው፤ ብሩና ወር​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ቃድ የቀ​ረበ ነው፤


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”


跟着我们:

广告


广告