Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 23:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እንዲሁም መባ ሆኖ የሚቀርበውን ገጸ ኅብስት፣ የእህል ቍርባኑን ዱቄት፣ ቂጣ የሚጋግሩ፣ የሚያቦኩና የሚሰፈረውንም ሆነ የሚለካውን ሁሉ በኀላፊነት የሚቈጣጠሩ እነርሱ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ደግሞም የተቀደሰ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቁርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በመለክያ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ ለሚቀርበው ኅብስትና ዱቄት፥ ያለ እርሾ ለሚጋገረው ቂጣና በወይራ ዘይት ለሚለወሰው ዱቄት ኀላፊዎች ሲሆኑ፥ ለቤተ መቅደስ መባ ሆኖ የሚቀርበውን ሁሉ የሚመዝኑና የሚለኩ እነርሱ ነበሩ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ደግሞም ገጸ ኅብስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በምጣድም ቢጋገር፥ ቢለወስም፥ ለእህል ቍርባን በሆነው በመልካሙ ዱቄት በመስፈሪያና በልክ ሁሉ ያገልግሉ ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 23:29
16 交叉引用  

ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታው ቆመው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገ​ንና ለማ​ክ​በር፥


በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።


ወደ ውስ​ጡም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገብ​ተው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሁሉ፥ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የኅ​ብ​ስተ ገጹ​ንም ገበ​ታና ዕቃ​ውን ሁሉ አን​ጽ​ተ​ናል፤


ስለ አም​ላ​ካ​ች​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት፥ ስለ ኅብ​ስተ ገጽም፥ ዘወ​ት​ርም በሰ​ን​በ​ትና በመ​ባቻ ስለ ማቅ​ረብ ስለ እህሉ ቍር​ባ​ንና ስለ​ሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት፥ ስለ በዓ​ላ​ትም፥ ስለ ተቀ​ደ​ሱ​ትም ነገ​ሮች፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስለ​ሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ር​የው ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥


በገ​በ​ታም ላይ ኅብ​ስተ ገጹን ሁል​ጊዜ በፊቴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።


በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ሮች ገን​ዘ​ቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ሚዛን ወሰደ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።


跟着我们:

广告


广告