Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 23:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮንን ዘሮች መርዳት፣ የቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሁሉ ማንጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 “ሥራቸውም የጌታን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ በሚሰጡተት አገልግሎት አሮንን ልጆች መርዳት፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት መሥራት ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ኀላፊነታቸውም የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በሚያከናውኑት ተግባር መርዳት፥ የአደባባዩንና የክፍሎቹን እንክብካቤ መጠበቅ፥ ንዋያተ ቅድሳትን ማንጻት፥ እንዲሁም አጠቃላይ የሆነውን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት ማከናወን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሥራቸውም የእግዚአብሔርን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ነበረ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 23:28
28 交叉引用  

በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።


የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ በከ​ሊ​ታ​ው​ያ​ንና በፈ​ሊ​ታ​ው​ያን ላይ ሹም ነበረ፤ የዳ​ዊ​ትም ልጆች በን​ጉሡ አጠ​ገብ አለ​ቆች ነበሩ።


በመ​ጨ​ረ​ሻ​ውም በዳ​ዊት ትእ​ዛዝ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት የሌዊ ልጆች ተቈ​ጠሩ።


ደግ​ሞም ገጸ ኅብ​ስት፥ ስስ ቂጣም ቢሆን፥ በም​ጣ​ድም ቢጋ​ገር፥ ቢለ​ወ​ስም ለእ​ህል ቍር​ባን በሆ​ነው በመ​ል​ካሙ ዱቄት በመ​ስ​ፈ​ሪ​ያና በልክ ሁሉ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ውስጥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ የሚ​ያ​ሠ​ሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድ​ስቱ ሺህም ጻፎ​ችና ፈራ​ጆች ነበሩ።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ክፍ​ላ​ቸ​ውን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ሥራ ሁሉ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በት ዕቃ ሁሉ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ ለሚ​ሆ​ነ​ውም፥


እነሆ፥ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ይህ ነው፤ በሰ​ን​በት ቀን ከም​ት​ገ​ቡት ከእ​ና​ንተ ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሦ​ስት አንድ እጅ በመ​ግ​ቢያ በሮች በረ​ኞች ሁኑ፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ግን ከካ​ህ​ና​ትና ከሌ​ዋ​ው​ያን ከሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አገ​ል​ጋ​ዮች በቀር ማንም አይ​ግባ፤ እነ​ርሱ ቅዱ​ሳን ናቸ​ውና ይግቡ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቅ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሰብ​ስ​በው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ንጉሡ ትእ​ዛዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያነጹ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን አነጹ።


እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ሌዋ​ው​ያን ሆይ፥ ስሙኝ፤ ራሳ​ች​ሁን አንጹ፤ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀድሱ፤ ርኩ​ስን ነገር ሁሉ ከመ​ቅ​ደሱ አስ​ወ​ግዱ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም የካ​ህ​ና​ት​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ሰሞን በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸ​ውና በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ በሮች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡና ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑም፥ ያከ​ብ​ሩም ዘንድ ካህ​ና​ቱ​ንና ሌዋ​ው​ያ​ኑን መደበ።


በካ​ህ​ና​ትና በሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች ፊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጓዳ​ዎች ውስጥ እስ​ክ​ት​መ​ዝኑ ድረስ ተግ​ታ​ችሁ ጠብቁ” አል​ኋ​ቸው።


ከይ​ሁ​ዳም ልጅ ከዛራ ወገን የባ​ስ​ያ​ዘ​ብ​ኤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በን​ጉሡ አጠ​ገብ ነበረ።


ዕቃ ቤቶ​ቹ​ንም እን​ዲ​ያ​ነጹ አዘ​ዝሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ​ዎች፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን፥ ዕጣ​ኑ​ንም መልሼ በዚያ አገ​ባሁ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።


ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


በደጀ ሰላ​ሙም በሁ​ለቱ ወገን በዚ​ህና በዚያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶ​ችና የተ​ቀ​ረጹ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​በት፤ የመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎ​ችና የእ​ን​ጨቱ መድ​ረክ እን​ዲሁ ነበሩ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አን​ጻር በሰ​ሜ​ንና በደ​ቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነ​ርሱ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ካህ​ናቱ ከሁሉ ይልቅ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ምግብ የሚ​በ​ሉ​ባ​ቸው ቤቶች ናቸው። ስፍ​ራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር፥ የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ቱ​ንና የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት ያኖ​ራሉ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሃ​ያው ክንድ አን​ጻር፥ በው​ጭ​ውም አደ​ባ​ባይ በወ​ለሉ አን​ጻር በሦ​ስት ደርብ በት​ይዩ የተ​ሠራ መተ​ላ​ለ​ፊያ ነበረ።


ነገር ግን ለአ​ገ​ል​ግ​ሎቱ ሁሉና በእ​ርሱ ውስጥ ለሚ​ደ​ረ​ገው ሁሉ የቤ​ቱን ሥር​ዐት ጠባ​ቂ​ዎች አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告