Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 22:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አን​ተም ብዙ ሠራ​ተ​ኞ​ችን፥ ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወቃ​ሪ​ዎ​ች​ንና ጠራ​ቢ​ዎ​ችን፥ ሥራ​ው​ንም ሁሉ ለማ​ድ​ረግ ጠቢ​ባን ሰዎ​ችን አብ​ዝ​ተህ ጨምር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ድንጋይ ጠራቢዎች፣ ግንበኞች፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች የሆኑ ብዙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ ሙያ የተጠበቡ ሰዎች አሉህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በአንተም ዘንድ ብዙ ሠራተኞች፥ ድንጋይ ወቃሪዎችና እንጨት ጠራቢዎች፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎች ሁሉ አሉህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንተ ብዙ ሠራተኞች ድንጋይ የሚፈልጡ፥ ግንበኞችና አናጢዎች፥ እንዲሁም ባለሙያዎች በየዐይነቱ አሉልህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በአንተም ዘንድ ብዙ ሠራተኞች፥ ድንጋይና እንጨት ወቃሪዎችና ጠራቢዎች፥ ሥራውንም ሁሉ ለማድረግ ጠቢባን ሰዎች ሁሉ አሉ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 22:15
10 交叉引用  

የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን፥ የዝ​ግባ እን​ጨ​ት​ንም፥ አና​ጢ​ዎ​ች​ንም፥ ድን​ጋይ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንም ላከ፤ ለዳ​ዊ​ትም ቤት ሠሩ​ለት።


እር​ሱም ከን​ፍ​ታ​ሌም ወገን የነ​በ​ረች የባል አልባ ሴት ልጅ ነበረ፤ አባ​ቱም የጢ​ሮስ ሰው ናስ ሠራ​ተኛ ነበረ፤ የና​ስ​ንም ሥራ ሁሉ ይሠራ ዘንድ በጥ​በ​ብና በማ​ስ​ተ​ዋል፥ በብ​ል​ሃ​ትም ተሞ​ልቶ ነበር። ወደ ንጉ​ሡም ወደ ሰሎ​ሞን መጥቶ ሥራ​ውን ሁሉ ሠራ።


አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።


ቍጥር በሌ​ለው በወ​ር​ቅና ብር፥ በና​ስና ብረት ተነ​ሥ​ተህ ሥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ነገር ግን ሰማ​ይና ከሰ​ማ​ያት በላይ ያለ ሰማይ ክብ​ሩን ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ለእ​ርሱ ቤት ይሠራ ዘንድ ማን ይች​ላል? በፊቱ ዕጣን ከማ​ጠን በቀር ቤት እሠ​ራ​ለት ዘንድ እኔ ማን ነኝ?


አሁ​ንም በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስና በብ​ረት፥ በሐ​ም​ራ​ዊና በቀይ፥ በሰ​ማ​ያ​ዊም ግምጃ መለ​በጥ የሚ​ች​ልና፥ አባቴ ዳዊት ካዘ​ጋ​ጃ​ቸው በእኔ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ካሉት ብል​ሃ​ተ​ኞች ጋር ቅርጽ ማው​ጣት የሚ​ያ​ውቅ ብል​ሃ​ተኛ ሰውን ላክ​ልኝ።


“ልብሰ መት​ከ​ፉ​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከተ​ፈ​ተለ ከቀይ ግምጃ በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ፥ የተ​ለየ የሽ​መና ሥራ ያድ​ርጉ።


በአ​ና​ጺ​ዎች ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ፥ የጥ​በ​ብ​ንም ሥራ ያስ​ተ​ውል ዘንድ፥ በወ​ር​ቅና በብር፥ በና​ስም ይሠራ ዘንድ፥


በአ​ን​ጥ​ረኛ፥ በብ​ልህ ሠራ​ተ​ኛም፥ በሰ​ማ​ያ​ዊና በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍ​ታም በሚ​ሠራ ጠላፊ፥ በሸ​ማ​ኔም ሥራ የሚ​ሠ​ራ​ውን፥ ማና​ቸ​ው​ንም ሥራና በብ​ል​ሃት የሚ​ሠ​ራ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ልብ ጥበ​ብን ሞላ።


跟着我们:

广告


广告