Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ዳዊት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ሰይፍ የተ​ነሣ ስለ ፈራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ወደ​ዚያ ይሄድ ዘንድ አል​ቻ​ለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ዳዊት የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ ወደዚያ ሄዶ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ዳዊት ግን የጌታን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደዚያ መሄድ አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ነገር ግን ዳዊት የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ ወደዚያ ሄዶ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን መልአክ ሰይፍ ስለ ፈራ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደዚያ ይሄድ ዘንድ አልቻለም።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:30
16 交叉引用  

በዚ​ያም ቀን ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራና፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት ትገ​ባ​ለች?” አለ።


በዚ​ያም ቀን ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኔ እን​ዴት አመ​ጣ​ለሁ?” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈራ።


ዳዊ​ትም ዐይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በም​ድ​ርና በሰ​ማይ መካ​ከል ቆሞ፥ የተ​መ​ዘ​ዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተዘ​ር​ግቶ አየ። ዳዊ​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም ማቅ ለብ​ሰው በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደፉ።


ሙሴም በም​ድረ በዳ የሠ​ራት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ በዚ​ያን ጊዜ በገ​ባ​ዖን ባለው በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ነበሩ።


ዳዊ​ትም፥ “ይህ የአ​ም​ላኬ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ነው፤ ይህም ለእ​ስ​ራ​ኤል ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ነው” አለ።


እጅ​ህን ከእኔ አርቅ፤ ግር​ማ​ህም አታ​ስ​ደ​ን​ግ​ጠኝ።


እኔ ባሰ​ብሁ ቍጥር እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ ጻዕ​ርም ሥጋ​ዬን ይይ​ዛል።


ስለ​ዚህ በፊቱ ደነ​ገ​ጥሁ፤ አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም የተ​ነሣ እፈ​ራ​ለሁ።


በመ​ን​ገ​ድህ ሁሉ ይጠ​ብ​ቁህ ዘንድ መላ​እ​ክ​ቱን ስለ አንተ ያዝ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፤ እንዲህም አለኝ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ፤


跟着我们:

广告


广告