Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን አዘ​ዘው፤ ሰይ​ፉ​ንም በአ​ፎቱ ከተ​ተው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም እግዚአብሔር ለመልአኩ ተናገረ፤ መልአኩም ሰይፉን ወደ አፎቱ መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጌታም መልአኩን አዘዘው፥ ሰይፉንም በአፎቱ ከተተው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔርም መልአኩን “ሰይፍህን ወደ አፎቱ መልስ” አለው፤ መልአኩም እንደታዘዘው አደረገ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔርም መልአኩን አዘዘው፤ ሰይፉንም በአፎቱ ከተተው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:27
12 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ያጠ​ፋት ዘንድ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከክ​ፉው ነገር ይቅር አላት፤ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፋ​ውን መል​አክ፥ “እን​ግ​ዲህ በቃህ፤ እጅ​ህን መልስ” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ አጠ​ገብ ቆሞ ነበረ።


የሦ​ስት ዓመት ራብ፥ ወይም ሦስት ወር የጠ​ላ​ቶ​ችህ ሰይፍ እን​ዲ​ያ​ገ​ኝህ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ መሰ​ደ​ድን፥ ወይም ሦስት ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ፥ ቸነ​ፈ​ርም በም​ድር ላይ መሆ​ንን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ሁሉ ማጥ​ፋ​ትን ምረጥ፤ አሁ​ንም ለላ​ከኝ ምን እን​ደ​ም​መ​ልስ አስ​ረ​ዳኝ” አለው።


ኦር​ናም ዘወር ብሎ ንጉሡ ዳዊ​ትን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተሸ​ሽ​ገው የነ​በሩ አራ​ቱን ብላ​ቴ​ኖ​ቹን አየ። ኦር​ናም ስንዴ ያበ​ራይ ነበር።


ዳዊ​ትም በዚያ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ጠራ፤ ከሰ​ማ​ይም ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሆ​ነው መሠ​ዊያ ላይ በእ​ሳት መለ​ሰ​ለት፤ እሳ​ቱም የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በላ።


በዚ​ያም ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ እንደ ሰማው ዳዊት ባየ ጊዜ፥ በዚያ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ።


ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።


አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ሆይ! ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገ​ባህ ግባ፤ ጸጥ ብለ​ህም ዕረፍ።


ወደ ሰገ​ባ​ውም መል​ሰው፤ በተ​ፈ​ጠ​ር​ህ​ባት ስፍራ አት​ደር፤ በተ​ወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር እፈ​ር​ድ​ብ​ሃ​ለሁ።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለው “ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስን፥ “ሾተ​ል​ህን ወደ አፎቷ መልስ፤ አብ የሰ​ጠ​ኝን ጽዋ ሳል​ጠጣ እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁን?” አለው።


መላ​እ​ክት ሁሉ መና​ፍ​ስት አይ​ደ​ሉ​ምን? የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይወ​ርሱ ዘንድ ስለ አላ​ቸው ሰዎ​ችስ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት ይላኩ የለ​ምን?


跟着我们:

广告


广告