1 ዜና መዋዕል 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ከመቅሠፍቱ ይቅር አለ፤ የሚያጠፋውንም መልአክ፥ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እንዲሁም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፋ መልአክ ላከ፤ መልአኩ ሊያጠፋትም ሲል እግዚአብሔር አይቶ ስለሚደርሰው ጥፋት ዐዘነ፤ ሕዝቡን የሚያጠፋውንም መልአክ፣ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 እግዚአብሔርም ለማጥፋት ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ላከ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ ጌታ አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተፀፀተ፥ የሚያጠፋውንም መልአክ፦ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የጌታም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ቀጥሎም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለመደምሰስ መልአክ ልኮ ነበር፤ ነገር ግን ኢየሩሳሌምን ማጥፋት እንደ ጀመረ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ያደረሰው ችግር አሳዝኖት መልአኩን “እስከ አሁን የደረሰባቸው ችግር ይበቃልና አቁም!” አለው። በዚያን ጊዜ መልአኩ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እግዚአብሔርም ያጠፋት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ሰደደ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተፀፀተ፤ የሚያጠፋውንም መልአክ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ፤” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር። 参见章节 |