Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ጋድን፥ “እነ​ዚህ ሦስት ነገ​ሮች እጅግ ይከ​ብ​ዱ​ኛል፥ እጅ​ግም ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ አሁ​ንም ምሕ​ረቱ ብዙ ነውና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ ይሻ​ለ​ኛል፤ በሰው እጅ ግን አል​ው​ደቅ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ታላቅ ስለ ሆነ፣ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻለኛል፤ በሰው እጅስ አልውደቅ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ዳዊትም ጋድን፦ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በጌታ እጅ ልውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም “እነሆ እኔ ለምርጫ በሚያስቸግር ሁኔታ ላይ ነኝ! ይሁን እንጂ በሰው እጅ መውደቅ አልፈልግም፤ እግዚአብሔር መሐሪ ስለ ሆነ እርሱ ራሱ ይቅጣኝ” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ጋድን “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ ልውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፤” አለው።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 21:13
31 交叉引用  

የኤ​ል​ሳ​ዕም ሎሌ ማለዳ ነቃ፤ ተነ​ሥ​ቶም በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ ጭፍ​ሮች ከተ​ማ​ዋን ከብ​በ​ዋት አየ። ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ። ሎሌ​ውም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እና​ድ​ርግ?” አለው።


ወደ ከተማ ብን​ገባ ራብ በከ​ተማ አለና፥ በዚያ እን​ሞ​ታ​ለን፤ በዚ​ህም ብን​ቀ​መጥ እን​ሞ​ታ​ለን። እን​ግ​ዲህ ኑ፥ ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር እን​ሂድ፤ በሕ​ይ​ወት ቢያ​ኖ​ሩን እን​ኖ​ራ​ለን፤ ቢገ​ድ​ሉ​ንም እን​ሞ​ታ​ለን” ተባ​ባሉ።


በዚ​ያም ዖዴድ የተ​ባለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማ​ር​ያም የሚ​መ​ጣ​ውን ጭፍራ ሊገ​ና​ኘው ወጣ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፤ “እነሆ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ስለ ተቈጣ በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እና​ን​ተም ወደ ሰማይ በሚ​ደ​ርስ ቍጣ ገደ​ላ​ች​ኋ​ቸው።


ወደ ተራ​ሮች ይወ​ጣሉ፥ ወደ ሜዳ፥ ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ህ​ላ​ቸው ስፍ​ራም ይወ​ር​ዳሉ፥


ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ የቀና መን​ገ​ድን መራ​ቸው።


እኔ ግን በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤ አን​ተን በመ​ፍ​ራት በቤተ መቅ​ደ​ስህ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።


ሰው እና​ታ​ችን ጽዮን ይላል፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ሰው ተወ​ለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠ​ረ​ታት።


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


በሕ​ዝቤ ላይ ተቈ​ጥቼ ነበር፤ ርስ​ቴ​ንም አረ​ከ​ስሽ፤ በእ​ጅ​ሽም አሳ​ልፌ ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ለሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸው አል​ራ​ራ​ሽም፤ ቀን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም እጅግ አክ​ብ​ደ​ሻል።


ክፉ ሰው መን​ገ​ዱን፥ በደ​ለ​ኛም ዐሳ​ቡን ይተው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለስ፤ እር​ሱም ይም​ረ​ዋል፤ እርሱ ብዙ በደ​ላ​ች​ሁን ይተ​ው​ላ​ች​ኋ​ልና።


ከሰ​ማይ ተመ​ለስ፤ ከቅ​ድ​ስ​ና​ህና ከክ​ብ​ርህ ማደ​ሪ​ያም ተመ​ል​ከት፤ ቅን​አ​ት​ህና ኀይ​ል​ህስ ወዴት ነው? የቸ​ር​ነ​ት​ህና የይ​ቅ​ር​ታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለ​ሃ​ልና።


በስ​ጦ​ታው ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ዐሰ​ብሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች እው​ነ​ተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸር​ነ​ቱና እንደ ጽድቁ ብዛ​ትም ይቅ​ር​ታ​ውን ያመ​ጣ​ል​ናል።


ያሳ​ዘ​ነ​ውን ሰው እንደ ይቅ​ር​ታው ብዛት ይም​ረ​ዋ​ልና፤


እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?”


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር።


በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ እኔስ ከዚህ ዓለም ልለይ፥ በከ​ክ​ር​ስ​ቶ​ስም ዘንድ ልኖር እወ​ዳ​ለሁ፤ ይል​ቁ​ንም ለእኔ ይህ ይሻ​ለ​ኛል፤ ይበ​ል​ጥ​ብ​ኛ​ልም።


በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ መው​ደቅ እጅግ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው።


跟着我们:

广告


广告