Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሰዎ​ችም ሄደው በሰ​ዎቹ ላይ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለዳ​ዊት አስ​ታ​ወ​ቁት። ሰዎ​ቹም በብዙ አፍ​ረ​ዋ​ልና ይቀ​በ​ሏ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን ላኩ፤ ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፥ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በሰዎቹ ላይ የደረሰባቸውን ዳዊት በሰማ ጊዜ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር፣ ወደ እነርሱ መልክተኞችን ላከ፤ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ቈዩና ከዚያ በኋላ ትመጣለችሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነርሱም ወደመጡበት ተመለሱ። ዳዊትም በሰዎቹ ላይ የተደረገውን በነገረሩት ጊዜ ሰዎቹ እጅግ ስላፈሩ እንዲቀበሏቸው መልእክተኞችን ላከ፤ ንጉሡም፦ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነርሱም ወደ ቤታቸው ለመመለስ አፈሩ፤ ዳዊት ስለ ሆነው ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ መልእክተኞች ልኮ በኢያሪኮ እንዲቈዩና ጢማቸው እስከሚያድግ ድረስ እንዳይመለሱ ነገራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወሬኞችም ሄደው በሰዎቹ ላይ የተደረገውን ለዳዊት አስታወቁት። ሰዎቹም በብዙ አፍረዋልና ተቀባዮች ላከ፤ ንጉሡም “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ ተመለሱ፤” አለ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 19:5
7 交叉引用  

ለዳ​ዊ​ትም ስለ ሰዎቹ ነገ​ሩት፤ ሰዎቹ እጅግ አፍ​ረው ነበ​ሩና ተቀ​ባ​ዮ​ችን ላከ። ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አላ​ቸው።


በእ​ር​ሱም ዘመን የቤ​ቴል ሰው አኪ​ያል ኢያ​ሪ​ኮን ሠራ፤ በነ​ዌም ልጅ በኢ​ያሱ ቃል እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ በበ​ኵር ልጁ በአ​ቢ​ሮን መሠ​ረ​ቷን አደ​ረገ፥ በታ​ናሹ ልጁም በዜ​ጉብ በሮ​ች​ዋን አቆመ።


ሐና​ንም የዳ​ዊ​ትን አገ​ል​ጋ​ዮች ወስዶ የጢ​ማ​ቸ​ውን ግማሽ አስ​ላ​ጫ​ቸው፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም እስከ ወገ​ባ​ቸው ድረስ ለሁ​ለት ቀድዶ ሰደ​ዳ​ቸው።


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ሰዎች እን​ዳ​ፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ፥ ከሶ​ርያ ሞዓካ፥ ከሱ​ባም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይቀ​ጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ላከ።


ባልንጀሮቹ የሆኑ ባሮችም ያደረገውን አይተው እጅግ አዘኑ፤ መጥተውም የሆነውን ሁሉ ለጌታቸው ገለጡ።


የራ​ሱም ጠጕር ከላ​ጩት በኋላ ያድግ ጀመር።


跟着我们:

广告


广告