Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ አንድ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞች ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ለመቶ ሰረ​ገ​ሎች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ብቻ አስ​ቀ​ርቶ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን ፈረ​ሶች ቋንጃ ቈረጠ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገላ፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኛና ሃያ ሺሕ እግረኛ ወታደር ማረከ፤ አንድ መቶ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ አስቀርቶ የቀሩትን ቋንጃቸውን ቈረጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሰረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊትም ለመቶ ሰረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሰረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቆረጠ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዳዊት የሀዳድዔዜርን አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ኻያ ሺህ እግረኛ ሠራዊት ማረከ፤ አንድ መቶ ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶችን ለራሱ አስቀርቶ የቀሩትን ፈረሶች ቋንጃ ቈረጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዳዊትም ከእርሱ አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረሰኞች፥ ሃያ ሺህም እግረኞች ወሰደ፤ ዳዊትም ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን ብቻ አስቀርቶ የሠረገሎቹን ፈረሶች ቋንጃ ቈረጠ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:4
11 交叉引用  

በም​ክ​ራ​ቸው ሰው​ነቴ አት​ገ​ና​ኛ​ቸው፤ ዐሳ​ቤም በአ​መ​ፃ​ቸው አት​ተ​ባ​በ​ርም፤ በቍ​ጣ​ቸው ሰውን ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ በገዛ ፈቃ​ዳ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ርን ሥር ቈር​ጠ​ዋ​ልና።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ።


ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።


የነ​በ​ሩ​ትም አለ​ቆች እነ​ዚህ ናቸው፥ የሳ​ዶቅ ልጅ ካህኑ ዓዛ​ር​ያስ፤


ዳዊ​ትም በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውን ግዛ​ቱን ለማ​ጽ​ናት በሄደ ጊዜ ሔማ​ታ​ዊ​ውን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።


ኢያ​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


跟着我们:

广告


广告