Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በዚ​ያም ሸለቆ ምሽግ ሠርቶ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፥ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱም በኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በኤዶምያስም የጦር ሠራዊት አሰፈረ፥ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል አድራጊ አደረገው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በመላው የኤዶም ግዛት ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሁሉ ስፍራ ድል አድራጊ አደረገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በኤዶምያስም ጭፍሮች አኖረ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ገባሮች ሆኑ። እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድል ይሰጠው ነበር።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:13
19 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


አሕ​ዛብ ይገ​ዙ​ልህ፤ አለ​ቆ​ችም ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ጌታ ሁን፤ የአ​ባ​ት​ህም ልጆች ይስ​ገ​ዱ​ልህ፤ የሚ​ረ​ግ​ምህ እርሱ ርጉም ይሁን፤ የሚ​ባ​ር​ክ​ህም ቡሩክ ይሁን።”


ይስ​ሐ​ቅም መለሰ ዔሳ​ው​ንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ ለእ​ርሱ ተገ​ዦች አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እህ​ሉን፥ ወይ​ኑ​ንና ዘይ​ቱ​ንም አበ​ዛ​ሁ​ለት፤ ለአ​ንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?”


በሰ​ይ​ፍ​ህም ትኖ​ራ​ለህ፤ ለወ​ን​ድ​ም​ህም ትገ​ዛ​ለህ፤ ነገር ግን ቀን​በ​ሩን ከአ​ን​ገ​ትህ ልት​ጥል ብት​ወ​ድድ ከእ​ርሱ ጋር ተስ​ማማ።”


በዚያ ጊዜም ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ።


ዳዊ​ትም ኤዶ​ም​ያ​ስን ባጠፋ ጊዜ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ኢዮ​አብ ተወ​ግ​ተው የሞ​ቱ​ትን ሊቀ​ብር በወጣ ጊዜ፥ የኤ​ዶ​ም​ያ​ስ​ንም ወንድ ሁሉ በገ​ደለ ጊዜ፥


ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ አቢሳ ከኤ​ዶ​ማ​ው​ያን በጨው ሸለቆ ውስጥ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች ገደለ።


ዳዊ​ትም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤ ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ያድ​ነው ነበር።


በኀ​ይ​ልህ ሰላም ይሁን፥ በክ​ብ​ርህ ቦታ ደስታ አለ።


አቤቱ፥ ፍጥ​ረ​ትህ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፥ ጻድ​ቃ​ን​ህም ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል።


ኤዶ​ም​ያ​ስም ርስቱ ይሆ​ናል፤ ጠላቱ ኤሳው ደግሞ ርስቱ ይሆ​ናል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በኀ​ይል ያደ​ር​ጋል።


በደ​ማ​ስቆ ከተማ ከን​ጉሥ አር​ስ​ጣ​ስ​ዮስ በታች የሆነ የአ​ሕ​ዛብ አለቃ ሊይ​ዘኝ ወድዶ የደ​ማ​ስ​ቆን ከተማ ያስ​ጠ​ብቅ ነበር።


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


ዮና​ታ​ንም በኮ​ረ​ብ​ታው የነ​በ​ሩ​ትን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ መታ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ያን ሰሙ፤ ሳኦ​ልም፦ እስ​ራ​ኤል ይስሙ ብሎ በሀ​ገሩ ሁሉ ቀንደ መለ​ከት ነፋ።


በነ​ጋም ጊዜ፥ የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ጋሻ ጃግ​ሬ​ውን፥ “ና፤ በዚያ በኩል ወዳ​ለው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር እን​ለፍ” አለው፤ ለአ​ባ​ቱም አል​ነ​ገ​ረ​ውም።


ዳዊ​ትም በአ​ካ​ሄዱ ሁሉ ብል​ህና ዐዋቂ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።


跟着我们:

广告


广告