Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እጅ እንዲነሣውና ደስታውንም እንዲገልጥለት ልጁን አዶራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ብዙ ጊዜ ጦርነት ገጥሞ ነበር። አዶራምም ከወርቅ፣ ከብርና ከናስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ዕቃዎች አመጣለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ድል ስለ አደረገው ደኅንነቱን እንዲጠይቀውና እንዲመርቀው ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት አድርጎ ስለ ነበር፥ ንጉሥ ዳዊትን እጅ እንዲነሣና በሀዳድዔዜር ላይ ስለ ተቀዳጀው ድል ደስታውን እንዲገልጥለት ልጁን ዮራምን ወደ ዳዊት ላከ። ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ዕቃዎችን ገጸ በረከት አድርጎ ለዳዊት አመጣለት፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁል ጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ወግቶ ስለ መታው ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ ይመርቀው ዘንድ ልጁን አዶራምን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የወርቅና የብር የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 18:10
6 交叉引用  

ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤


ንጉ​ሡም ዳዊት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ከኤ​ዶ​ምና ከሞ​ዓብ፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም ከማ​ረ​ከው ብርና ወርቅ ጋር እነ​ዚ​ህን ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ።


የኤ​ማ​ትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን፥ ጭፍ​ራ​ው​ንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ።


የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ዝና በሰ​ማች ጊዜ በግ​መ​ሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ሰሎ​ሞ​ንን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ አጫ​ወ​ተ​ችው።


በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።


跟着我们:

广告


广告