Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 17:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ኸው ከሕ​ዝ​ብህ ፊት አሕ​ዛ​ብን በማ​ሳ​ደድ ታላ​ቅና የከ​በረ ስምን ለአ​ንተ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ለአ​ን​ተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ መራ​ኸው እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ሌላ ሕዝብ የለም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከግብጽ ተቤዥተህ እንዳወጣኸው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ ማን አለ? እነርሱ እግዚአብሔር ለራሱ ሊቤዣቸው ከምድር ሕዝቦች መካከል የመረጣቸው ናቸው፤ በሕዝብህም ፊት ታላላቅና አስፈሪ ነገሮችን በማድረግ መንግሥታትን በፊታቸው አሳደድህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ስምህን እንዳስጠራህ፥ ለአንተም ሕዝብ እንዲሆን ለመቤዠት እንደ ሄድህለት እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕዝብህ እስራኤል ከየትኛው ሕዝብ ጋር ይነጻጸራል? አንተ እግዚአብሔር ከባርነት ነጻ አውጥተህ የራስህ ሕዝብ ያደረግኸው በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን? ሕዝብን ከግብጽ ለማስወጣት በመታደግህና በታላላቅ ሥራዎችህ ስምህን ታላቅና ገናና አደረግኸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አንተ እግዚአብሔር ከግብጽ ካወጣኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብን በማሳደድ በታላቅና በሚያስፈራ ነገር ለአንተ ስም ታደርግ ዘንድ፥ ለአንተም ሕዝብ ትቤዥ ዘንድ እንደ ሄድህለት እንደ አንተ ሕዝብ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ሌላ ሕዝብ አለን?

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 17:21
29 交叉引用  

አቤቱ፥ እን​ዳ​ንተ ያለ የለም፤ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአ​ንተ በቀር አም​ላክ የለም።


ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝ​ብህ አደ​ረ​ግ​ኸው፤ አን​ተም አቤቱ፥ አም​ላክ ሆን​ሃ​ቸው።


እንደ ታበ​ዩ​ባ​ቸ​ውም ዐው​ቀህ ነበ​ርና በፈ​ር​ዖ​ንና በባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ፥ በም​ድ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ተአ​ም​ራ​ትን አሳ​የህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስም​ህን አስ​ጠ​ራህ።


ክብ​ሬም ይመ​ለ​ስ​ል​ኛል፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ እነ​ሣ​ለሁ፤ ማል​ጄም እነ​ሣ​ለሁ፤


በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤ ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።


ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


ስለ ስሜ ቍጣ​ዬን አሳ​ይ​ሃ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ህም ግር​ማ​ዬን አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ።


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


የክ​ብ​ር​ህ​ንም ሥራ ባደ​ረ​ግህ ጊዜ፥ ተራ​ሮች በፊ​ትህ ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በብ​ርቱ እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣህ።


አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ን​ጠ​ራው ጊዜ ሁሉ እን​ደ​ሚ​ቀ​ር​በን፥ አም​ላኩ ወደ እርሱ የቀ​ረ​በው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ።


跟着我们:

广告


广告