1 ዜና መዋዕል 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታንን፥ “እነሆ፥ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጣለች” አለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን፦ “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የጌታም ቃል ኪዳን ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ንጉሥ ዳዊት በዚህ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ነበር፤ አንድ ቀን ንጉሡ ነቢዩን ናታንን አስጠርቶ “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል!” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል፤” አለው። 参见章节 |