Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




1 ዜና መዋዕል 15:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በዚህ ሁኔታ መላው የእስራኤል ሕዝብ በሆታ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፣ ጸናጽል እየጸነጸሉ፣ መሰንቆና በገና እየደረደሩ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ፥ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲሁ እስራኤል ሁሉ “ሆ!” እያሉ፥ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል መሰንቆና በገና እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።

参见章节 复制




1 ዜና መዋዕል 15:28
16 交叉引用  

ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ በእ​ል​ልታ ቀንደ መለ​ከት እየ​ነፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አመ​ጡ​አት።


ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።


ዳዊ​ትና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ዘ​ም​ራን ጋር በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በከ​በሮ፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በመ​ለ​ከት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይዘ​ምሩ ነበር።


ዳዊ​ትም በዜማ ዕቃ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም እን​ዲ​ያ​ዜሙ፥ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በደ​ስታ ከፍ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ መዘ​ም​ራ​ኑን “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሹሙ” ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ተና​ገረ።


ካህ​ና​ቱም ሰበ​ንያ፥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ ናት​ና​ኤል፥ ዓማ​ሣይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ በና​ያስ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት መለ​ከት ይነፉ ነበር። አብ​ዲ​ዶ​ምና ኢያ​ኤ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በረ​ኞች ነበሩ።


ዳዊ​ትም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሌዋ​ው​ያ​ንም ሁሉ፥ መዘ​ም​ራ​ኑም፥ የመ​ዘ​ም​ራ​ኑም አለቃ ኮኖ​ን​ያስ የጥሩ በፍታ ቀሚስ ለብ​ሰው ነበር፤ ዳዊ​ትም የከ​በረ ልብስ ለብሶ ነበረ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ረ​ሰች ጊዜ የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮል በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ ንጉ​ሡም ዳዊት ሲዘ​ፍ​ንና ሲጫ​ወት አይታ በል​ብዋ ናቀ​ችው።


ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር በተ​መ​ረቀ ጊዜ ምረ​ቃ​ውን በደ​ስ​ታና በም​ስ​ጋና፥ በመ​ዝ​ሙ​ርም፥ በጸ​ና​ጽ​ልም፥ በበ​ገ​ናም፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ለማ​ድ​ረግ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ኑን በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ሁሉ ፈለጉ።


መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም ያዛ​ቸው፥ እንደ ወላ​ድም በዚያ አማጡ።


ከተ​ማ​ቸው በረሃ ትሁን፥ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ አይ​ገኝ፤


跟着我们:

广告


广告